Get Mystery Box with random crypto!

ሐናና ኢያቄም ሐናና ኢያቄም በስለት ያገኙሽ/፪/ ድንግል እናታችን በጣም ደስ ይበልሽ/፪/ ኧኸ | የማህበር መዝሙር 🙏🙏🙏

ሐናና ኢያቄም


ሐናና ኢያቄም በስለት ያገኙሽ/፪/
ድንግል እናታችን በጣም ደስ ይበልሽ/፪/ ኧኸ

ለመዳን ምክንያት ድንግል አንቺ ነሽ/፪/
ንጽሕት ቅድስት እያልን እናመስግንሽ/፪/ኧኸ

በቤተ መቅደስ ኖርሽ በቅድስና/፪/
እየተመገብሽ ሰማያዊ መና/፪/ ኧኸ

ዕፁብ ነው ድንቅ ነው የአምላካችን ሥራ/፪/
የሰጠን ድንግልን እንዳናይ መከራ/፪/ ኧኸ