የምስራች ተወለደች እሰይ እሰይ የምስራች ተወለደች እሰይ እሰይ የምድር እና የሰማይ ንግስት ተወለደች የዓለም እመቤት ተወለደች የአምላክ እናት አዝ----- ሃና እና እያቄም ወለዱ ሰማይ እሰይ እሰይ መፅናኛ እንድትሆነን ለአዳም ዘር ሲሳይ እሰይ እሰይ ሊባኖስ ተራራ ቃልን ተናገሪ እሰይ እሰይ የድንግልን ልደት ዘላለም መስክሪ እሰይ እሰይ አዝ----- የሰው ልጆች ደስታ የምህረት ደውል እሰይ እሰይ ከያዕቆብ ድንኳን የወጣች ድንግል እሰይ እሰይ ነይ ከሊባኖስ ከአንበሶች መኖሪያ እሰይ እሰይ ተስፋን ያየንብሽ የልዑል ማደሪያ እሰይ እሰይ አዝ----- እያቄም ፀሎትህ ሃና ልመናሽ እሰይ እሰይ ይሄው መልስ አገኘ ሰምሯል ስለትሽ እሰይ እሰይ እፁብ ድንቅ ብለው ፍጥረታት ዘመሩ እሰይ እሰይ ተወልዳለች እና የአምላክ መንበሩ እሰይ እሰይ አዝ----- ካህናት ተነሱ ድንግልን አክብሩ እሰይ እሰይ ፅዮንን ክበቧት ቅጥሮቿንም ዙሩ እሰይ እሰይ አወድሷት ሁሌም ብፅዕት እያላችሁ እሰይ እሰይ የልጇ በረከት ይገባል ቤታችሁ እሰይ እሰይ 299 views15:50