ተወልዳለችና ========== ተወልዳለችና የጌታ እናት የእኛ መድኃኒት እናመስግናት እናወድሳት እንውደዳት/2/ የአዳምን ሕይወት አ.ዝ----------------------// አዳም ሲሰደድ ከጥንት እርስቱ ፊቱን ሸፈነው ጭንቀት ፍርሃቱ እያለቀሰ ገነትን ሲያጣ ተስፋ አንቺ ሆንሽው የመዳኑ ዕጣ አ.ዝ-----------------------// ሊባኖስ ተራራ ተሰማ ዜና ምሥራቅ ወለዱ እያቄም ወሐና ዳግማዊት ሄዋን ምክንያተ ድህነት ልደቷን ሰማን በቅድስት እለት አ.ዝ------------------// የልደትሽ ቀን ልደታችን ነው በአንቺ ነውና ልጅ የተባልነው ፋራን የተባልሽ ቅድስት ተራራ በአንቺ መወለድ ዓለሙ በራ 291 views15:49