Get Mystery Box with random crypto!

ሸብሻቦ ማርያም : #በስም_አጠራርሽ በስም አጠራርሽ ልቤ ሐሴት አደረገ መንፈሴ ተፅናና ው | የማህበር መዝሙር 🙏🙏🙏

ሸብሻቦ ማርያም :
#በስም_አጠራርሽ

በስም አጠራርሽ ልቤ ሐሴት አደረገ
መንፈሴ ተፅናና ውዳሴሽን እየፈለገ
ምን እሆን ነበር አንቺን ባይሰጠኝ ኖሮ
እመብርሃን ደስታዬ ነሽ የሰላሜ ኑሮ
#አዝማች
መወለድሽን ስሰማ ሳቅ እና ደስታ ከበበኝ
ምስራቹን አግኝቼ ሳቅና ለቅሶ ቀረ ተረሳኝ
ጭንቀቴ ተለወጠ ትንቢቱ እውን ሲሆን
ሊባኖስ ተራራ ላይ ስምሽን ሳመሰግን
ልደትሽን ልደታ ብዬ አከብራለሁ
የአምላክ እናት መልካም ዜናዬ እልሻለሁ
#አዝማች
በቤተ መቅደስ ሳይሽ የዋህቱ ሙሽራዬ
ሰርጌን ደግሼ ባንቺ ወይን ተሞላ ጕዳዬ
ህብስተ ሰማይ በላሁ ከማህፀንሽመሶብ
ሐምራዊ በፍታ ለብሼ ክብሩን አይቼ ስጠግብ
ልደትሽ ልደታ ብዬ አከብራለሁ
የአምላክ እናት መልካም ዜናዬ እልሻለሁ
#አዝማች
ፋናሽን ተከትዬ ገሊላ ድረስ ተጉዤ
በግርግም ተገኘሁኝ የልጅሽንመዳፍይዤ
ልክ እንደ ከርቤ ሽቶ ስምሽ መአዛዬ ሆነ
ማርያም ብሎ አፌ ገፀ ምድርንም ሸፈነ
ልደትሽን ልደታ ብዬ አከብራለሁ
የአምላክ እናት መልካም ዜናዬ እልሻለሁ
#አዝማች
ከቀስቱ ሥር እንዳመልጥ አንቺ ነሽ ለኔ ምልክቴ
በበረከት እንድኖር ገብተሻል ከምስኪኑ ቤት
ይሄው ዘመን ለማለም ሌላ ትምክህት የለኝም
ልፅናና ተደግፌሽ በመከራ ቀን ሳልደክም
ልደትሽን ልደታ ብዬ አከብራለሁ
የአምላክ እናት መልካም ዜናዬ እልሻለሁ

#ዮም_ፍስሐ_ኮነ

ዮም ፍስሐ ኮነ ፍስሐ ኮነ
በእንተ ልደታ ለማርያም

በባርነት ሳለን ፍስሐ ኮነ
ሀጢአት ባለም ነግሳ " "
በድንግል መወለድ " "
ቀረልን አበሳ " "
እግዚአብሄር መረጠሽ " "
ልትሆኝ እናቱ " "
ይኸው ተፈፀመ " "
የዳዊት ትንቢቱ " "
#አዝ
የሰው ልጆች ተስፋ ፍስሐ ኮነ
የአዳም ህይወት " "
የኢያቄም የሀና " "
ፍሬ በረከት " "
ምክንያተ ድሂን " "
ኪዳነ ምህረት " "
ድንግል ተወለደች " "
የጌታየ እናት " "
#አዝ
በሄዋን ምክንያት ፍስሐ ኮነ
ያጣነውን ሰላም " "
ዛሬ አገኘነው " "
በድንግል ማርያም " "
የምስራች እንበል " "
ሀዘናችን ይጥፋ " "
ተወልዳለች እና " "
የዓለም ሁሉ ተስፋ " "