✟ድንግል ተወለደች✟ ድንግል ተወለደች እመቤታችን ከዳዊት ዘር ወጣች ተስፋስንቃችን የቴክታ ዸጥሪቃ ህልማቸው ተፈታ ከድቅድቅ ጨለማ ጨረቃዋወጥታ ከሴም ከያእቆብ ከብሩካን ሀገር ከቅዱስ ተራራ ወጣች ከአሮን ዘር የጽድቅ ሀመልማሏ ዳዊት ቤት በቀለች አዳምን የሚያድን በረከት አዝላለች አዝ__ ዝናብ ያየንባት የጽድቅ ደመና ድንግል ተወለደች ከኢያቄምከሀና ከእሴይ በትርስር ወጥቷል አበባዋ በድንግል ተፈታ የሔዋን መርገሟ አዝ__ ምድር ተደሰተች ቀረባት ሰማዩ ሊያበቃ ነውና የአዳም ስቃዮ በድንግል መወለድ ሆነ ተድላደስታ ዮም ፍስሀ ኮነ በማርያም ልደታ አዝ___ ድንግል ስትወለድ ሊባኖስ አበራ በደስታ ተሞላ ታላቁ ተራራ ቀስተደመና ናት ሰማያዊ ንስር ገና እንዘምራለን ስለድንግል ክብር 188 viewsedited 15:46