✟ልደታ ለማርያም✟ ልደታ ለማርያም ስምሽ ስንጠራ መላ አካላታችን ለመለመ አፈራ/2/ ከገነት የፈለቅሽ ልዩ መአዛችን የቃላችን ቃና ናርጎስ ወዛችን በጉዛችን ሁሉ ስምሽን አስከትለን እንቅፋት ሳይነካን/2/ ከእርስቱ እንገባለን አዝ____ ቃልኪዳን እንዳለ ስምሽን ለጠራ ዘወትር ይድናል ከክፋ መከራ ልደታ ለማርያም ስምሽን ስንቅ አድርገን ምን አለ ያጣነው/2/ አንቺን ተስፋ አድርገን አዝ____ በወንጌል አጸዶች ዙርያሽን ተከበሽ የዜማ አውአፍ ቀን ከሊት ሲቀኙሽ የዘካርያስ እጣን ምድርን ያሻተተ ነፍሳችን ተነጥቆ/2/ ካንቺ ሊኖር ሻተ አዝ____ እንደምን ያለ ክብር እንዴት ያለ ግርማ የጥበብ መገኛ የዜማ አውድማ የሚዘራ ወንጌል ከደጊቱ መሬት ሰላሳና ስልሳ/2/ የመቶ ፍሬው አዝ____ በእናት ፊት ማደግ ሰቆቃ የለበት ሳይጠይቁት ሰጪ የልብ አውቃ እመቤት ስምሽን ለመጥራት ለዚህ ያበቃሽን ድንግል ማርያም ሆይ/2/ ከቁጥር አታጉዲይን 218 views15:46