Get Mystery Box with random crypto!

#ማርያም_ፊደል_ናት ወደ ቀድሞ ነገር እንመለስ የአምላክን እናት እናወድስ ከፍቅሯ እርቃችሁ የ | የማህበር መዝሙር 🙏🙏🙏

#ማርያም_ፊደል_ናት

ወደ ቀድሞ ነገር እንመለስ
የአምላክን እናት እናወድስ
ከፍቅሯ እርቃችሁ የምትኖሩ
ማርያም ፊደል ናት ኑ ተማሩ



ቃል ተጽፎባታል የመዳኛ ፊደል
ጥበብ የሚሞላ ጨለማን የሚሰቅል
ለቃል ሥጋ መሆን ምክንያት ስለሆነች
ቀርባችሁ ተማሩ ማርያም ፊደል ነች

#አዝ

አዲሱ ቃል ኪዳን ከላይ የተፃፈው
በገሊላ ናዝሬት ገብርኤል ያበሰረው
በማርያም እቅፍ ላይታገኙታላችሁ
የምሥጢር መዝገቡን አንብቡ ገልጣችሁ

#አዝ

ያዘለችው ወንጌል ቃሉ ይፈውሳል
አምኖ ላነበበው ነፍስ ያለመልማል
በጀርባዋ ያለው እግዚአብሔር ነውና
አቅርቡ ለማርያም ውዳሴ ምስጋና

#አዝ

ብዙዎች ተማሩ ስሟን እየጠሩ
በአባታቸው መንግስት እንደፀሐይ በሩ
ክብር ልዕልናዋን ገብርኤል ነግሮናል
ካወደሷት ጋራ ለክብሯ ቆመናል