Get Mystery Box with random crypto!

.... የኒካሕ መስፈርቶች 1. የተጋቢዎቹን ስም ለይቶ መግለፅ፡- ከአንድ በላይ ልጆች ባሉበት | መወዳ ቻናል(MEWEDA CHANNEL)

.... የኒካሕ መስፈርቶች

1. የተጋቢዎቹን ስም ለይቶ መግለፅ፡- ከአንድ በላይ ልጆች ባሉበት ሁኔታ “ልጄን አጋብቼሃለሁ” ወይም ለልጅህ አጋብቼያለሁ” ቢል በቂ አይሆንም፡፡ ስለዚህ ስም ተጠቅሶ ለምሳሌ “ልጄን ፋጢማን ለዐብደላህ አጋብቼያለሁ” ሊል ነው፡፡

2. የሁለቱ ተጋቢዎች ስምምነት፡- የግዴታ ጋብቻ ተቀባይነት የለውም፡፡

[ቡኻሪ፡ 5136፣ ሙስሊም፡ 1419]

3. ለሴቷ ወልይ መኖር፡፡ ነብዩ ﷺ “ያለ ወልይ ኒካሕ የለም” ብለዋልና፡፡

[ሶሒሕ ኢብን ማጃህ፡ 1537]

4. ኒካሑ ሲታሰር ሁለት ብቁ ምስክሮች መኖራቸው፡፡ [ሶሒሕ ኢብን ሒባን፡ 4075]
5. ተጋቢዎቹን እንዳይጋቡ የሚከለክል ነገር (ቅርብ ዝምድና፣ አማችቻ፣ ጥቢ፣ የእምነት ልዩነት፣ …) አለመኖር፡፡


...የኒካሕ ማእዘናት

1. ጋብቻን ከሚከለክሉ ነገሮች ነፃ የሆኑ ተጋቢዎች

2. ከሴቷ ወልይ በኩል “አጋብቻለሁ” ወይም መሰል የይሁንታ ቃል

3. የአግቢው ወይም ወኪሉ “ተቀብያለሁ” ወይም መሰል የመስማማት ቃል

ከአልፊቅሁል ሙየስሰር ኪታብ የተወሰደ

https://t.me/mewedachannel