Get Mystery Box with random crypto!

بسم الله الرحمن الرحيم አላህ ሰዎችንም ሆነ አጋንንትን የፈጠረው እርሱን ብቻ እ | መወዳ ቻናል(MEWEDA CHANNEL)

بسم الله الرحمن الرحيم

አላህ ሰዎችንም ሆነ አጋንንትን የፈጠረው እርሱን ብቻ እንዲያመልኩ፣ ለርሱ ብቻ በሚገቡ የአምልኮ አይነቶችን እንዲያከናውኑና አንድንም ፍጡር እንዳያጋሩ መሆኑን በግልፅ ቋንቋ ተናግሯል::

وَمَا خَلَقْتُ الْجِنَّ وَالْإِنسَ إِلَّا لِيَعْبُدُونِ [٥١:٥٦]

“ጋኔንንና ሰውንም ሊግገዙኝ እንጅ ለሌላ አልፈጠርኳቸውም”

አላህ ቁርአን በማውረድና ነቢዩን (ሰለሏሁ ዐለይሂ ወሰለም) በመላክ የአምልኮን ምንነት አይነቶቹንና የአፈፃፀም ስርዓቶቹን በዝርዝር አስረድቷል::

ሶላት ፣ዘካ ፣ፍራቻ ፣ክጀላ ፣ልመና፣ መመካት፣ እርድ፣ ስለትና ሌሎችም የአምልኮ ክፍሎችን ለአላህ ብቻ ማድረግ የ “ላ ኢላሀ ኢለሏህ” መዞሪያ ዛቢያ ሲሆን ከአምልኮ ክፍሎች ቅንጣት ያህል ቢሆን እንኳ ከርሱ ውጭ ለነቢይ፣ለመላኢኮች፣ለጂን፣ለመሻይኾችም ሆነ ለማንኛውም ፍጡር ማዋል ሽርክ ነው።

አላህ እንዲህ ይላል:-

قُلْ إِنَّمَا أَنَا بَشَرٌ مِّثْلُكُمْ يُوحَىٰ إِلَيَّ أَنَّمَا إِلَٰهُكُمْ إِلَٰهٌ وَاحِدٌ ۖ فَمَن كَانَ يَرْجُو لِقَاءَ رَبِّهِ فَلْيَعْمَلْ عَمَلًا صَالِحًا وَلَا يُشْرِكْ بِعِبَادَةِ رَبِّهِ أَحَدًا [١٨:١١٠]

««እኔ አምላካችሁ አንድ አምላክ ብቻ ነው ማለት ወደኔ የሚወረድልኝ ቢጤያችሁ ሰው ብቻ ነኝ፡፡ የጌታውንም መገናኘት የሚፈልግ ሰው፤ መልካም ሥራን ይሥራ፡፡ በጌታውም መገዛት አንድንም አያጋራ» በላቸው፡፡

يَا أَيُّهَا النَّاسُ اعْبُدُوا رَبَّكُمُ الَّذِي خَلَقَكُمْ وَالَّذِينَ مِنْ قَبْلِكُمْ لَعَلَّكُمْ تَتَّقُونَ (21) الَّذِي جَعَلَ لَكُمُ الْأَرْضَ فِرَاشًا وَالسَّمَاءَ بِنَاءً وَأَنْزَلَ مِنَ السَّمَاءِ مَاءً فَأَخْرَجَ بِهِ مِنَ الثَّمَرَاتِ رِزْقًا لَكُمْ فَلَا تَجْعَلُوا لِلَّهِ أَنْدَادًا وَأَنْتُمْ تَعْلَمُونَ (22)

““እናንተ ሰዎች ሆይ! የፈጠራችሁን እነዚያንም ከናንተ በፊት የነበሩትን (የፈጠረውን) ጌታችሁን ተገዙ፤ (ቅጣትን) ልትጠነቀቁ ይከጀላልና፡፡ (እርሱ) ያ ለናንተ ምድርን ምንጣፍ ሰማይንም ጣራ ያደረገ ነው፤ ከሰማይም (ከደመና) ውሃን ያወረደ በርሱም ከፍሬዎች ለናንተ ሲሳይን ያወጣ ነው፡፡ እናንተም (ፈጣሪነቱን) የምታውቁ ስትኾኑ ለአላህ ባላንጣዎችን አታድርጉ”

فَاعْبُدِ اللَّهَ مُخْلِصًا لَهُ الدِّينَ (2) أَلَا لِلَّهِ الدِّينُ الْخَالِصُ

““አላህንም ሃይማኖትን ለእርሱ ብቻ ያጠራህ ኾነህ ተገዛው፡፡ ንቁ! ፍጹም ጥሩ የኾነው ሃይማኖት የአላህ ብቻ ነው”

قُلْ إِنَّ صَلَاتِي وَنُسُكِي وَمَحْيَايَ وَمَمَاتِي لِلَّهِ رَبِّ الْعَالَمِينَ (1622) لَا شَرِيكَ لَهُ وَبِذَلِكَ أُمِرْتُ وَأَنَا أَوَّلُ الْمُسْلِمِينَ (163)

««ስግደቴ፣ መገዛቴም፣ ሕይወቴም፣ ሞቴም ለዓለማት ጌታ ለአላህ ነው» በል፡፡ «ለእርሱ ተጋሪ የለውም፡፡ በዚህም (በማጥራት) ታዘዝኩ፡፡ እኔም የሙስሊሞች መጀመሪያ ነኝ» (በል)፡፡

“አላህን ብቻ ተገዙ ከርሱ ሌላ በአምልኮው ማንንም አታጋሩ” የሚለው የተውሒድ ጥሪ የቁርአን ሙሉ መልእክትና የመላው ነቢይና መልክተኛ የስብከት አጀንዳ በመሆኑ ከየትኛውም የእውቀት ዘርፍ በማስቀደም ተውሂድን መገንዘብና ተግባራዊም ማድረግ አማራጭ የሌለው ግዴታ ነው::

አላህን ብቻ በማምለክ ከስሜትና ከሸይጧን ተገዥነት እንዲሁም ምንም ጥቅም ሊያስገኝም ሆነ አንዳችም ጉዳት ሊመክት ከማይችል የባሪያ ባርነት ነፃ ሆኖ በዚህች ዓለም የተረጋጋ ህይወት ከመኖርም በተጨማሪ ዘላለማዊ ደስታና የማይቋረጥ እድል የተሟላበትን ጀነት መጎናፀፊያ ሰበብ ይረጋገጣል::


https://t.me/mewedachannel