Get Mystery Box with random crypto!

••●◉ የ'ኔ መጨረሻ ◉●•• አምና ወዳጆቿ... ሙዚቃ መዉደዷን ሲያወጉ ሰምቼ | For ethios መፀሀፍ, ትረካ, አጫጭር ታሪኮች 📚📜📓🚵🇪🇹🇪🇹🇪🇹🇪novels, 🇹ethiopians books

••●◉ የ'ኔ መጨረሻ ◉●••

አምና ወዳጆቿ...
ሙዚቃ መዉደዷን ሲያወጉ ሰምቼ
ካሴት አዉጥቻለሁ አመቱን ለፍቼ
''አንባቢ ነች'' ሲሉ ሆኛለሁ ፀሀፊ
ጥቂት ጠብቄያለሁ ሆኜ ልብስ ሰፊ
አጥር ለማጠንከር ግንበኛ ሆኛለሁ
እግሯንም ለመንካት ጫማ ጠርጌያለሁ
እሷን ለመማረክ ቀን ይገኛል ብዬ
ያልሆንኩትን ስሆን እሷን ተከትዬ
ዛሬ ዕድሉ ቀንቶኝ ከፊቷ ቆሜያለሁ
ሰርጓን ልቀርፅላት ካሜራ ይዣለሁ።