Get Mystery Box with random crypto!

.......// አለማወቅ \\ በጥቂት ቃል ብዙ አጠፋሁ፤ እሳት ልሳን እየተፋሁ። | For ethios መፀሀፍ, ትረካ, አጫጭር ታሪኮች 📚📜📓🚵🇪🇹🇪🇹🇪🇹🇪novels, 🇹ethiopians books

.......// አለማወቅ \\
በጥቂት ቃል ብዙ አጠፋሁ፤
እሳት ልሳን እየተፋሁ።
ተናጋሪ እሾህ ምላስ፤
መልካም ነገር ማያንተራስ።
እሳት ከእሾህ የሚተፋ፤
ማንስ ቀርቦት እየፈራ።
ግን እላለሁ ብቸኝነት ይገባኛል፤
ፃድቅ ሳለሁ
ማንስ ቀርቦ ይዘልፈኛል።
ስህተት ነቃሽ ደግሞ አስተዋይ፤
ከሺህ መልካም
ክፉን ብቻ ቀድሞ የሚያይ።
የንስር አይን የተባለ፤
ድካም ነቅሶ የሰው
ሞራል እየጣለ።
ሳይ'ገባኝ ወይ ብሞካሽ
ብወደስም፤
የራሴን ምስ
ጎራ ይዤ ብነጠልም።
ብወድቅ ጊዜ ቀን ቢጥለኝ፤
እንደ ሀጥአኑ እንደምሆን
ይህ እጣዬን ማን ነገረኝ ።

#abela_black