Get Mystery Box with random crypto!

#Update በደቡብ ክልል ከሚገኙት ዞኖችና ልዩ ወረዳዎች ውስጥ የ ' ክላስተር ' አደረጃጀትን | Mereja today news

#Update

በደቡብ ክልል ከሚገኙት ዞኖችና ልዩ ወረዳዎች ውስጥ የ " ክላስተር " አደረጃጀትን ባለማጽድቅ ብቸኛ የሆነው የጉራጌ ዞን ምክር ቤት አስቸኳይ ጉባኤውን ነገ ሐሙስ ነሐሴ 5/2014 እንደሚያካሂድ ተገልጿል።

የአስቸኳይ ጉባኤውን መጠራት የዞኑ ምክር ቤት አፈ ጉባኤ አርሽያ አህመድ እንዳረጋገጡ ኢትዮጵያ ኢንሳይደር በድረገፁ አስነብቧል።

ድረገፁ አነጋግሬያቸዋለሁ ያላቸው ሶስት የጉራጌ ዞን ምክር ቤት አባላት በነገው አስቸኳይ ጉባኤ ላይ እንዲገኙ ጥሪ እንደተላለፈላቸው ገልጸዋል።

የጉራጌ ዞን ምክር ቤት 97 አባላት ያሉት ሲሆን ከእነርሱ ውስጥ ስድስቱ የኢትዮጵያ ዜጎች ለማህበራዊ ፍትህ (ኢዜማ) ተመራጮች ናቸው።

ቀሪዎቹ የምክር ቤት አባላት ገዢው ብልጽግና ፓርቲን ወክለው የተወዳደሩ እና ምክር ቤቱን የተቀላቀሉ ናቸው። 

ከዚህ በፊት በነበረው ልማድ ጉባኤው ከመካሄዱ ጥቂት ቀናት ቀደም ብሎ የጉባኤውን አጀንዳዎች በያዘ ደብዳቤ ጥሪ ይደረግላቸው እንደነበር የሚያስታውሱት የም/ ቤት አባላት የአሁኑ ስብሰባ አጀንዳ ግን እንዳልተገለጸላቸው ተናግረዋል።

ስማቸው እንዲጠቀስ ያልፈለጉ አንድ የዞኑ ምክር ቤት አባል፤ የነገው አስቸኳይ ጉባኤ ዋና አጀንዳ " የአደረጃጀት ጉዳይ " ሊሆን እንደሚችል ግምታቸውን አስቀምጠዋል።

የነገውን ጉባኤ ዋነኛ አጀንዳ ምን እንደሆነ ጥያቄ የቀረበላቸው የዞኑ ም/ቤት አፈ ጉባኤ፤ " አጀንዳ ለምክር ቤት አባላት ብቻ ነው የሚገለጸው " የሚል ምላሽ ሰጥተዋል።

Credit : www.ethiopiainsider.com