Get Mystery Box with random crypto!

#Gambella • 2 ሰዎች ተገድለዋል። • 1 ሰው ቆስሎ ሆስፒታል ህክምና ላይ ነው። • 2 ህ | Mereja today news

#Gambella

• 2 ሰዎች ተገድለዋል።
• 1 ሰው ቆስሎ ሆስፒታል ህክምና ላይ ነው።
• 2 ህፃናት ታፍነው ተወስደዋል።

በጋምቤላ ከደቡብ ሱዳን የሚነሱ የ "ሙርሌ ጎሳ" ታጣቂዎች ድንበር አቋርጠው በመግባት ጥቃት አድርሰዋል።

በዲማ ወረዳ ኡኩጉ የስደተኛ መጠለያ ጣቢያ ላይ ድንበር ተሻግረው በመጡ የሙርሌ ታጣቂዎች በከፈቱት ተኩስ የ2 ሰው ህይወት ሲያልፍ አንድ ሰው ቆስሎ 2 ህፃናት በታጣቂዎች መወሰዳቸውን የክልሉ ፖሊስ አሳውቋል።

ታጣቂዎች ጥቃቱን የፈፀሙት ከትናንት በስቲያ ከምሽቱ 4:30 ላይ ሲሆን ክልሉ በአሁኑ ሰዓት ልዩ ኃይሉንና ሚሊሻ በመጠቀም ሰላምና ፀጥታ የማስከበር ስራውን እየሰራ መሆኑን አሳውቋል።

ጥቃት አድራሾች ላይ እርምጃ ለመውሰድም በትኩረት እየተሰራ እንደሚገኝ ፖሊስ ገልጷል።

#ድንበሩ_ሰፊ ከመሆኑ ጋር ተያይዞ ተመሳሳይ ጥቃት እንዳይፈጸም መንግስት ከሚያደርገው ጥረት በተጓዳኝ ህብረተሰቡ በንቃት አካባቢውን እንዲጠብቅ ማሳሰቢያ ተላልፏል።

የጋምቤላ ፖሊስ ፥ በፀጥታ አካላት ከሚሰራው የመከላከል ስራ ጎን ለጎን የክልሉ መንግስት ከፌዴራል መንግስት ጋር በመሆን ለችግሩ ዘላቂ መፍትሄ ለማበጀት ከደ/ሱዳን መንግስት ጋር ውይይት እየተደረገ ነው ማለቱን ከክልሉ ፕሬስ ሴክሬተሪያት ያገኘነው መረጃ ያሳያል።