Get Mystery Box with random crypto!

#KenyaElection የኬንያን ምርጫ እየታዘቡ የሚገኙ #ኢትዮጵያውያን እነማን ናቸው ? ኬን | Mereja today news

#KenyaElection

የኬንያን ምርጫ እየታዘቡ የሚገኙ #ኢትዮጵያውያን እነማን ናቸው ?

ኬንያ እያካሄደች ያለችውን 5ኛው ዙር ፕሬዝዳንታዊ ምርጫ ለመታዘብ ኢትዮጵያውያን ኬንያ ይገኛሉ።

አቶ ኃይለማርያም ደሳለኝ ፦

የቀድሞ የኢትዮጵያ ጠቅላይ ሚኒስትር ኃለማርያም ደሳለኝ መቀመጫውን ደቡብ አፍሪካ ያደረገውን 'ብሬንትረስት ፋውንዴሽን'ን በመወከል ምርጫውን እየታዘቡ ናቸው።

አቶ ኃይለማርያም በሚመሩት ልዑክ ውስጥ እውቁ ኡጋንዳዊ ፖለቲከኛ እና ሙዚቀኛ ቦቢ ዋይን ይገኝበታል።

ዶ/ር ሙላቱ ተሾመ ፦

የቀድሞው የኢትዮጵያ ፕሬዝዳንት ዶክተር ሙላቱ ተሾመ ደግሞ የምሥራቅ አፍሪካ የልማት በየነ መንግሥታት (ኢጋድ) ታዛቢ ቡድንን በመምራት ኬንያ ናቸው።

ፕ/ር መረራ ጉዲና ፦

የተቃዋሚው የኦሮሞ ፌደራሊስት ኮንግረስ ፓርቲ መሪ እና አንጋፋው ፖለቲካኛ ፕሮፌሰር መረራ ጉዲና በኬንያ ተገኝተው ምርጫውን እየታዘቡ ይገኛሉ።

ሌንሳ ቢየና ፦

የኢትዮጵያ የህግ ባለሙያ ሴቶች ማህበር ዋና ስራ አስፈጻሚ ሌንሳ ቢየና የኤን ዲ አይ/አይ አር አይ (NDI/IRI) ዓለም-አቀፍ ምርጫ ታዛቢ ልኡክ አካል ሆነው በኤልዶሬት ከተማ በዩዜን ጊሹ ካዉንቲ የሚደረገዉን ምርጫ በመታዘብ ላይ ይገኛሉ፡፡

መረጃው ከቢቢሲ እና ከኢትዮጵያ የህግ ባለሙያ ሴቶች ማህበር ያገኘነው ነው።