Get Mystery Box with random crypto!

በህይወታችን በተደጋጋሚ ከምንፈፅማቸው ፀያፍ ስህተቶች ውስጥ አንዱ የሌሎችን ሚስጥር መዝራት ነው። | ሚንሃጁል ሀቅ(منهج الحق)

በህይወታችን በተደጋጋሚ ከምንፈፅማቸው ፀያፍ ስህተቶች ውስጥ አንዱ የሌሎችን ሚስጥር መዝራት ነው። የሚገርመው የራሳችን ሚስጥር ያመንነው ሰው ለሌላ ቢያወጣብን የማንወድ ሆነን ሳለ ለሌሎች አለመታመናችን ነው። አስገዳጅ ሁኔታ ካልገጠመ በስተቀር የሌላን ሰው ሚስጥር ለባልም ይሁን ለሚስት፣ ለቅርብም ይሁን ለሩቅ ማውጣት አይገባም። የጓደኛውን ሚስጥር እንደ ዋዛ ለሚስቱ ይነግራል። ሚስቱ ለቅርብ ጓደኛዋ፣ ያቺ ደግሞ ለሌላ ቅርብ ጓደኛዋ ወይም ለባሏ፣ ... እያለ ያደባባይ ሚስጥር ይሆናል። የቤቷን መከፋት ለጓደኛዋ ትነግራለች። ወ/ሮ ጓደኛ ለባሏ፣ እሱ ለጓደኛው፣ ... እያለ መጨረሻ መቆራረጥ፣ መቀያየም ያስከትላል። ከዚህ አይነት ጥፋት የሚተርፈው ከስንት አንድ ነው። ከመሰል ጥፋቶች ላይ ላለመውደቅ ይህንን የነብዩን (ﷺ) ሐዲሥ ማስታወስና መተግበር ተገቢ ነው፦
لا يُؤْمِنُ أحَدُكُمْ، حتّى يُحِبَّ لأخِيهِ ما يُحِبُّ لِنَفْسِهِ
{አንዳችሁ ለራሱ የሚወደውን ለወንድሙ እስከሚወድ ድረስ አያምንም።} [ቡኻሪ]

ሚስጥርህ እንዲጠበቅ ትውዳለህ ኣ? እንግዲያውስ የሌሎችን ሚስጥር ጠብቅ። ለራስህ የምትጠላውንም በወንድምህ ላይ አትፈፅም። ሚስጥርህ ወጥቶ ማግኘት እንደማትፈልግ ነጋሪ አያሻም። ልክ እንዲሁ ወንድምህም ሚስጥሩን ስትዘራበት ድንገት ቢደርስ ምን እንደሚሰማው አሰብ። ያመንከው እንዲከዳህ እንደማትፈልገው አንተም ላመነህ ታመን። የስነ ምግባር፣ የሞራል ቁንጮ የሆኑት ውዱ ነብይ (ﷺ) እንዲህ ይላሉ፦
أدِّ الأمانةَ إلى منِ ائتمنَكَ، ولا تخُنْ من خانَكَ
"አምኖ ለሰጠህ አማናውን አድርስ። የካደህን አትካድ።] [አሶሒሐህ፡ 423]
=
ኢብኑ ሙነወር
https://t.me/IbnuMunewor