Get Mystery Box with random crypto!

++++++++++++++++++++ ሆሣዕና.... ወደ ኢየሩሳሌም፥ ቤተ ፋጌ ሲደርስ፤ የታሰረች አህያ | መንፈሳዊ ግጥሞች ዘ ኦርቶዶክስ ተዋህዶ

++++++++++++++++++++
ሆሣዕና....
ወደ ኢየሩሳሌም፥ ቤተ ፋጌ ሲደርስ፤
የታሰረች አህያ፥
ፈተው እንዲያመጡ፥ ላካቸው ክርስቶስ።
እነዚህ ለጌታ፥ ያስፈልጋሉና፤
የታሰረችውን፥ አምጡልኝ ፍቱና።
ኢየሩሳሌም ሆይ፥ ላሳየሽ በጎነት ላሳየሽ ትህትና፤
እልል በይ ዘምሪ፥ እያልሽ ሆሣዕና።

አዳኝና ትሁት፥ ፃድቅ ንጉስሽ፤
በውርንጫ ጀርባ፥ መቷል አዳኝሽ።
ዘንባባ አንጥፉ፥ ህፃናትም ውጡ፤
አሁን አድን በሉት፥ ምስጋናችሁን ስጡ።
ሆሣዕና....
ደግሞም በዚያችው ቀን፥ ከመቅደስ ገባና፤
የሻጮችን ዙፋን፥ ገለበጠውና።
የወንበዴዎች ዋሻ፥ ያረጉትን ቤቱን፤
ርግብ ሻጩን ሰዶ፥ አፀዳ መቅደሱን።
የገንዘብ ለዋጩን፥ ወንበር ገለበጠ፤
በመቅደሱ ዙፋን፥ ጌታ ተቀመጠ።

ከሚጠቡትም አፍ፥ ምስጋና አዘጋጀ፤
አምላክነቱንም፥ ለአለም አወጀ።
የምትቀድሙ የምትከተሉ፥ ሆሣዕና እያላችሁ፤
በአርያም ይሰማ፥ መዝሙር እልልታችሁ።

አቤቱ ጌታ ሆይ፥ አሁን አድን በሉት፤
ልብሳችሁን ዘርጉ፥ ዘምባባ አንጥፉለት።
አሁን አድን ብለን፥ ወተናል በመንፈስ፤
በውርንጫ ጀርባ፥ አምላካችን ሲደርስ።
የዘካርያስ ትንቢት፥ አልቀረም ተፈቷል፤
በውርንጫ ጀርባ ፥ንጉሳችን መቷል።
+++++++++++++++++++++
@Menfesawigetmoch
ታዜና
" የሚቀድሙትም የሚከተሉትም። ሆሣዕና፤ በጌታ ስም የሚመጣ የተባረከ ነው፤"
(የማርቆስ ወንጌል 11:9)