Get Mystery Box with random crypto!

! ጠብቅ...! ! ተዋህዶ እምነትህን፣ ቤተክርስቲያንህን፣ የአርባ ቀን ቤትህን፣ አንዲት ስስትህን፣ | መንፈሳዊ ግጥሞች ዘ ኦርቶዶክስ ተዋህዶ

!
ጠብቅ...!
!
ተዋህዶ እምነትህን፣
ቤተክርስቲያንህን፣
የአርባ ቀን ቤትህን፣
አንዲት ስስትህን፣
የደም ስርህን፣
እናት አለምህን፣
ስም የሰጠችህን፣
ልጅ ያረገችህን።
!
ጠብቅ...!
!
አባት ካህንህን፣
የሚባርክህን፣
የሚናዝዝህን፣
ይፍታህ የሚልህን፣
ግርማ ሞገስህን፣
የሲኖዶስህን፣
የፓትሪያርክህን፣
ዶግማ ቀኖናህን፣
እምነት ማተብህን።
!
ጠብቅ...!
! አታስነጥቅ።
++++
አንድ ቤተክርስቲያን
አንድ ሲኖዶስ
አንድ ፓትሪያርክ
አንድ መንበር
++++++
ታዜና
      #መንፈሳዊ_ግጥሞች
      t.me/Menfesawigetmoch