Get Mystery Box with random crypto!

አትፍራ መሞት ነው ፥ከእግዜር የሚያደርሰው፣ የእስጢፋኖስ ዘመድ ፥ነውና ምንሆነው፣ የአርሴማ ዘመድ | መንፈሳዊ ግጥሞች ዘ ኦርቶዶክስ ተዋህዶ

አትፍራ መሞት ነው ፥ከእግዜር የሚያደርሰው፣
የእስጢፋኖስ ዘመድ ፥ነውና ምንሆነው፣
የአርሴማ ዘመድ ነውና ምንሆነው፣
የቂርቆስ ዘመድ ነውና ምንሆነው፣
የሐዋርያት ዘመድ ነውና ምንሆነው።
ዋኖቻችን ሁሉ ፥እንዲህ ነው ያለፉት፣
የክብር አክሊልን፥ በሞት ነው ያገኙት።

እናት ተዋህዶ፣ ዛሬ ትጣራለች፣
እንደ አባቶቻችን ፥ጠብቁኝ ትላለች።
++++
አንድ ቤተክርስቲያን
አንድ ሲኖዶስ
አንድ ፓትሪያርክ
አንድ መንበር