Get Mystery Box with random crypto!

ዲያቆን ዳንኤል ወንድሙ ቻ

የቴሌግራም ቻናል አርማ menamaedot — ዲያቆን ዳንኤል ወንድሙ ቻ
የቴሌግራም ቻናል አርማ menamaedot — ዲያቆን ዳንኤል ወንድሙ ቻ
የሰርጥ አድራሻ: @menamaedot
ምድቦች: ያልተመደበ
ቋንቋ: አማርኛ
ተመዝጋቢዎች: 1.20K
የሰርጥ መግለጫ

ይህን መጸሐፍ ብላ ሕዝ 3 ÷ 1
ይህ የቴሌግራም ቻናል የኔ የዲ/ን ዳንኤል ወንድሙ ነው
#በዚህ ቻናል ኦርቶዶክሳዊ አስተምህሮቶች ይለቀቃሉ ሁላችሁም ስለ ቀናች ኦርቶዶክሳዊት ተዋህዶ ለማወቅ ቤተሰብ ይሁኑ
ስለ ፕሮግራሙ አስተያየት ካሎት በውስጥ መስመር ያናግሩን

Ratings & Reviews

4.50

2 reviews

Reviews can be left only by registered users. All reviews are moderated by admins.

5 stars

1

4 stars

1

3 stars

0

2 stars

0

1 stars

0


የቅርብ ጊዜ መልዕክቶች 3

2022-06-26 17:32:10 https://m.facebook.com/story.php?story_fbid=1320195198509225&id=100009750105989
887 views14:32
ክፈት / አስተያየት ይስጡ
2022-06-08 21:26:48 https://vt.tiktok.com/ZSdGDJLyn/?k=1
1.1K views18:26
ክፈት / አስተያየት ይስጡ
2022-06-08 17:26:01 https://vt.tiktok.com/ZSdGhUxHM/?k=1
1.1K views14:26
ክፈት / አስተያየት ይስጡ
2022-06-07 00:03:15 https://vt.tiktok.com/ZSdsy3PE6/?k=1
912 views21:03
ክፈት / አስተያየት ይስጡ
2022-06-04 11:34:55 ከኃጢአት ባርነት ነጻ ወጥተን በመንፈሳዊ ልደት የእግዚአብሔር ልጆች የሆንበት አምላካችን ኢየሱስ ክርስቶስ ሐመረነ ዘኢይቀርቦ ሞገድ : ሞገድ የማይቀርበው መርከባችን ነው
በርግጥም የዲያቢሎስን ኃይል የሚገዛ የሞትን ሞገድ ዝም የሚያሰኝ እውነተኛ መረከብ እርሱ ነው ስለሆነም የሞት ሞገድ ያልቻለው ዓለም ሁሉ ከሲዖል ወደ ገነት ከባርነት ወደ ነጻነት ከጠላትነት ወደ ወዳጅነት የተሻገርንበት አውነተኛ መርከብ ኢየሱስ ክርስቶስ
877 views08:34
ክፈት / አስተያየት ይስጡ
2022-06-03 19:53:39 ✥ቅድስት ቤተ ክርስቲያናችን የጌታን ሥጋና ደም የምታከብርባቸው ዐሥራ አራት ቅዳሴያት አሏት፡፡ ከእነዚህ ምስጋናዎች መካከል ለዛሬው የቅዱስ ዲዮስቆሮስን የቍርባን ምስጋና እንደሚከተለው ይዘንላችሁ ቀርበናል፡፡ ጸሎቱና በረከቱ ከሁላችን ጋራ ይኑር ለዘለዓለሙ አሜን።

✥ቅዱስ ዲዮስቆሮስ በቅዳሴው ስለ ሐልዎተ እግዚአብሔር እንደዚህ
ይላል፡- እግዚአብሔር ከዓለም በፊት እስከ ዘለዓለምም ድረስ፤ እግዚአብሔር በሦስትነቱ አለ፣ እግዚአብሔር በመለኮቱ፣ እግዚአብሔር በመንግሥቱ አለ ። ከጎሕና ከጽባሕ በፊት፣ ከመዓልትና ከሌሊት በፊት፣ መላእክት ሳይፈጠሩ እግዚአብሔር በመንግሥቱ አለ።

✥ሰማያት ሳይዘረጉ፣ የየብስም ፊት ሳይታይ፣ ሐመልማላት ሳይበቅሉ
እግዚአብሔር በመንግሥቱ ነበረ ፡፡ ከፀሓይና ከጨረቃ፣ ከከዋክብትም በፊት፣ ከብርሃናትም መመላለስ በፊት እግዚአብሔር በመንግሥቱ ነበረ፡፡ ከሚንቀሳቀሱ እንስሳት በፊት፣ ከሚበሩም አዕዋፍ በፊት፣ ከባሕር አራዊት በፊት እግዚአብሔር በመንግሥቱ ነበረ ፡፡ አዳምን በርሱ አምሳልና አርኣያ ሳይፈጥረው፣ ትእዛዛቱንም ሳያፈርስ እግዚአብሔር በመንግሥቱ ነበረ ፡፡ ለአብ ለወልድ ለመንፈስ ቅዱስ ምስጋና ይገባል፤ ዛሬም ዘወትርም ለዘለዓለምም፡፡

✥ስለ ጌታችን ወደዚህ ዓለም መምጣት፣ ከቅድስት ድንግል ማርያም
ስለመወለዱ፣ ስለ አስተዳደጉ፣ ስለ አስተማረው ትምህርት፣ በገዳመ
ቆሮንቶስ ስለመጾሙ፣ ስለእኛ ስለተቀበለው መከራ፣ በሞቱ ሞታችንን ድል ስለመንሣቱ ፣ ስለትንሣኤው እንዲሁም ስለ ዕርገቱና ዳግም ምጽአቱ ደግሞ እንዲህ ብሏል፡- ሰማይ ይስማ ምድርም ታድምጥ የምድር መሠረቶችም ይደንግጡ ፡፡ በአባቱ ፈቃድ ወረደ ፣ በማርያም ዘንድ እንግዳ ሆነ፣ እግዚአብሔር በንጹሕ ድንግልናዋ ተወለደ ፡፡ በእንስሳት በረት ተጨመረ፣ የንጉሡንም እጅ መንሻ ተቀበለ፣ ከእናቱ ጡቶች ምግብን እየለመነ እንደ ሕፃናት አለቀሰ ፡፡ በግልጥ ተመላለሰ፣ እንደ ሰውም ታየ፣ በየጥቂቱ አደገ፣ በሠላሳ ዘመን በዮርዳኖስ ተጠመቀ።
እንደሰው ሆኖ ለመጾም በገዳም አደረ፣ ከዲያብሎስ ዘንድ ተፈተነ፣ የጨለማን መኳንንት በአምላክነቱ ኃይል ሻረ ። ሰውን የፈጠረ እርሱ እጁን ለሕማም ዘረጋ፣ አዳምን ከኀጢአት ቀንበር ነጻ ያድርገው ዘንድ፡፡ ወዳንተ ወደ አባቱ ወደ ሰማይ አቅንቶ አየ፣ አመሰገነ፣ ባረከ፣ ቆረሰም። ንጹሓን
ቅዱሳን ወገኖቹ ለሆኑ ደቀ መዛሙርቱ ለሐዋርያት ሰጣቸው፤ ይህ ኅብስት ለኀጢአት ማስተሥረያ ስለናንተ የሚፈተት ሥጋዬ ነው ንሡ ብሉ አላቸው ። ዳግመኛም ውኃውን ከወይን ጋራ ቀላቅሎ አመሰገነ፣ ባረከ፣ አከበረ ፡፡ ንጹሓን፣ ቅዱሳን ወገኖቹ ለሆኑ ደቀ መዛሙርቱ ለሐዋርያት ሰጣቸው ይህ ጽዋ ለብዙ ሰዎች ቤዛ ስለናንተ የሚፈስ ደሜ ነው ንሡ ጠጡ አላቸው ፡፡ አይሁድ ያዙት፣ የመላእክት ሠራዊት በመፍራትና በመንቀጥቀጥ የሚቆሙለት እርሱን በዐደባባይ አቆሙት። በእንጨት ላይ ሰቅለው በቀኖት ቸነከሩት፣ ራሱንም በዘንግ መቱት፣ ጎኑን በጦር
ወጉት፣ ለጉበኞች እስራኤል ካንድ ድንጋይ ያጠጣቸውን ለጥሙ ከከርቤ ጋራ የተቀላቀለ ሐሞትን አጠጡት፡፡

✥የማይሞት እርሱ ሞተ፤ ሞትን ይሽረው ዘንድ ሞተ፤ ሙታንን ያድናቸው ዘንድ ሞተ፤ በቃል ኪዳን ተስፋውን እንደ ነገራቸው ፡፡ ከእንጨት አወረዱት፣ በበፍታም ገንዘው በአዲስ መቃብር ቀበሩት፡፡ በሦስተኛው ቀን ከሙታን ተለይቶ ተነሣ፣ የተሰበሰቡ ደቀመዛሙርቱ ወዳሉበትም
ገባ፣ በጽርሐ ጽዮንም ታያቸው፣ በአርባኛውም ቀን ወደ ሰማይ ባረገ ጊዜ የአብን ተስፋ ደጅ ጥኑ ብሎ አዘዛቸው ፡፡ በአምሳውም ቀን በእሳት አምሳል መንፈስ ቅዱስን ሰደደላቸው፣ በአገሩ ሁሉ ቋንቋ ተናገሩ፣ እንደነርሱም ወደዚህ ኅብስትና ጽዋ ያንን ቅዱስ መንፈስህን ላክ፡፡
የጌታችንና የመድኃኒታችን የኢየሱስ ክርስቶስን ሥጋና ደም ያደርገው ዘንድ ለዘለዓለሙ፡፡

✥አንተ ሥጋዬን የበላ ደሜንም የጠጣ ከእኔ ጋራ ይኖራል እኔም
ከርሱ ጋራ እኖራለሁ እንዳልህ፡፡ ለሕይወትና ለዘለዓለም ከኃጢአት ለማንጻት ይሆናቸው ዘንድ ለወገኖችህ ሁሉ አንድ አድርገህ ስጥ ፡፡
የአንተ በሚሆን በመንፈስ ቅዱስ አንድ እንሆን ዘንድ መሆንን ስጠን፤ በዚህም ጵርስፎራ (ኅብስት) አድነን ለዓለሙ ሁሉ በምትሆን በአንተ ለዘለዓለሙ ሕያዋን እንሆን ዘንድ ፡፡ የእግዚአብሔር ስሙ ምስጉን ነው፣ በእግዚአብሔር ስም የሚመጣውም ምስጉን ነው፣ የጌትነቱ ስም ይመስገን ይሁን ይሁን የተመሰገነ ይሁን ፡፡ በሌላም በኩል ስለ ምሥጢረ ቁርባንንም በሰፊው ይነግረናል። ሥጋውና ደሙ ከምሥጢረ ሥጋዌ ጋር ያለውን ግንኙነት፤ ለመዳን ምሥጢራቱን መፈጸም እንዳለብን፤ ስለ ኢየሱስ ክርስቶስም አምላክነት፣ ንጉሥ መሆኑን፣ የሁሉ ገዢ መሆኑንና መሃሪነቱን እንደሚከተለው ይነግረናል፡- በግዕ ይምጣ በዓይናችን እንድናየው፣ በእጃችንም እንድናርደው በርሱ ደስ ይለን ዘንድ፡፡ ሥጋው ከዚህ ኅብስት ጋራ አንድ ይሁን፤ ደሙም በዚህ ጽዋ ይቀዳ ፡፡ ከኛ ወገን ላንዱ ይህን ኅብስት በሚበላበት ጊዜ ያለ ደምና ያለ መንፈስ ሥጋን
ብቻ የሚበላ፤ ይህንንም ጽዋ በሚጠጣበት ጊዜ ከኛ ወገን ላንዱ ያለ ሥጋና ያለ መንፈስ ደምን ብቻ የሚጠጣ አይምሰለው፣ ሥጋና ደም መንፈስም አንድ ናቸው እንጂ መለኮቱ ከትስብእቱ (ከሰውነቱ) ጋራ አንድ እንደሆነ ለዘለዓለሙ።

✥ዳግመኛም ሁሉን የሚይዝ የጌታችን የመድኃኒታችን የኢየሱስ ክርስቶስን አባት እግዚአብሔርን እንማልዳለን፤ ልመናችንን አልናቀምና አልተቆጣምና፣ ይቅርታውንም ከኛ አላራቀምና አምላካችን እግዚአብሔር ይቅር ባይ ስለሆነ፡፡

አዎን አቤቱ የሁሉ አምላክ ነህ፡፡
አዎን አቤቱ የሁሉ ንጉሥ ነህ ፡፡
አዎን አቤቱ ሁሉን የያዝህ ነህ ፡፡
አዎን አቤቱ ሁሉን የምትገዛ ነህ ፡፡
አዎን አቤቱ ሁሉን የምታድን ነህ ፡፡
አዎን አቤቱ በእውነት የሁሉ ገዢ ነህ ፡፡
አዎን አቤቱ የሁሉ መድኃኒት ነህ ፡፡
አዎን አቤቱ ሁሉን የምትጠብቅ ነህ ፡፡
አዎን አቤቱ ሁሉን የምትመግብ ነህ ፡፡

✥የልጅህን ሥጋ ከኛ ሥጋ ጋራ አንድ እንዳደረግህ፤ ያንተን መሢሕ ደምም ከኛ ደም ጋራ አንድ እንዳደረግህ እንዲሁ አንተን መፍራትን በልቦናችን፤ በጎ አምልኮትህንም በኅሊናችን ጨምር ፡፡ ሥጋውያን የምንሆን እኛ ግን የሥጋን ሕግ እናስባለን፤ የሥጋንም ሥራ እንሠራለን፤ በሥጋ መንገድም እንሄዳለን፡፡ አንተ ግን የመንፈስን ሥራ አስተምረን፤ የመንፈስንም ሕግ አስረዳን፤ የመንፈስንም መንገድ ምራን ፡፡ እኛን ኃጥአንን ብትምረን ያን ጊዜ መሐሪ ትባላለህና፡፡ ጻድቃንን ግን ከሥራቸው
የተነሣ ትምራቸዋለህ፣ እንደ ጽድቃቸውም ትሰጣቸዋለህ ፡፡ የቀደመ በደላችንን አታስብብን፤ አቤቱ ይቅርታህ ፈጥኖ ይደረግልን ፡፡ ወደ አንተ እንጮሃለን፤ ወደ አንተ እናለቅሳለን፤ ወደ አንተ እንማልዳለን ለዘለዓለሙ፡፡

✥አንብሮ ዕድ/ ካህኑ ሊባርክ ከመውጣቱ በፊት ለዘለዓለሙ የማይጠፋ የሕይወት ብርሃን እግዚአብሔር ወንዶቹንና ሴቶቹን ባሮችህን ተመልከታቸው፡፡ ስምህን መፍራትን በልቡናቸው ዝራ፤ በበረከት ያፈሩ
ዘንድ፤ ሥጋህና ደምህ ከተሰጣቸውም ጋራ ቁጠራቸው ፡፡ እጅህም በላያቸው የሚያድር ይሁን፤ እራሳቸውን በፊትህ ዝቅ ዝቅ ባደረጉ
በወገኖችህ ላይ በወንዶቹና በሴቶቹ በሽማግሎዎቹና በሕፃናቱ፤ በደናግልና በመነኰሳቱ በባልቴቶችና አባት እናት በሞተባቸው ላይ ፡፡
እኛንም ከዚያ ጨምር፤ ሠውርና እርዳ፣ አጽና፣ በመላእክትህ አለቆችም ኃይል አበርታ፡፡ ከክፉ ሥራ ሁሉ አርቀን፤ በበጎውም ሥራ ሁሉ አንድ አድርግ ፡፡ በአንድ ልጅህ በእርሱ ያለ ክብርና ጽንዕ ላንተ ይገባል፤ ከርሱ ጋራ ከመንፈስ ቅዱስም ጋራ፤ ✥ዛሬም ዘወትርም ለዘለዓለሙ አሜን።✥
893 views16:53
ክፈት / አስተያየት ይስጡ
2022-05-20 18:13:23 https://www.facebook.com/samuel.tezera.58/videos/1181210052637885/
782 views15:13
ክፈት / አስተያየት ይስጡ
2022-05-17 14:29:17
898 views11:29
ክፈት / አስተያየት ይስጡ
2022-05-10 09:35:10
1.0K views06:35
ክፈት / አስተያየት ይስጡ
2022-04-24 12:22:41
1.1K views09:22
ክፈት / አስተያየት ይስጡ