Get Mystery Box with random crypto!

ለመስጠት መሰጠት ያስፈልጋል! በአመት 10.2 ሚሊየን ዶላር የሚያገኘው የሴኔጋሉ የፊት አጥቂ ማኔ | መልካምነት ለራስ ነው!!!🌹🌹🌹

ለመስጠት መሰጠት ያስፈልጋል!

በአመት 10.2 ሚሊየን ዶላር የሚያገኘው የሴኔጋሉ የፊት አጥቂ ማኔ የተሰነጣጠቀና የተጫጫረ አይፎን ይዞ መታየቱ አነጋጋሪ ሆኖ ነበር፤ ስለሁኔታው የተጠየቀው ማኔ የሰጠው መልስ ግን አስደናቂ ነበር።

"10 ፌራሪ፣ 20 የዳይመንድ ሰአት እና 2 ጄት ፕሌንስ ምን ይሠሩልኛል? ለአለምስ ትርፋቸው ምንድነው? ድህነትን አይቼያለሁ. . .ተርቤ አቃለሁ፣ በባዶ እግሬም እጫወትም ነበር፣ ወደ ት/ቤትም አልገባሁም፡፡ አሁን ግን ሰዎችን መርዳት ችያለሁ።

የኔ ምርጫ ት/ቤቶችን መገንባት እና የተቸገሩትን ማልበስና መመገብ ነው፡፡ ለከፋ ድህነት ላሉ ሰዎች ልብስ፣ ጫማ እና ምግብ አቀርባለሁ፣ በተጨማሪም በጣም ድሃ ከሆነው የሴኔጋል ክልል ለሚመጡ ሰዎች ሁሉ የበኩሌን አስተዋጽኦ ለማድረግ በወር ለእያንዳንዳቸው 70 ዩሮ እሰጣለሁ። ቅንጡ ቤት፣ መኪና እና ፕሌን አያስደስቱኝም፤ ለህዝቤ ህይወት ከሰጠችኝ ማካፈሉ ነው የኔ ደስታ፡፡

ሁላችንም ችግርን እናውቀዋለን ችግሩ ግን ያንን ችግር ስናለፈው የመጣንበትን የፈተና ጉዞና የተቸገርነው ችግር ሲያልፍልን ችግርን እንረሳዋለን እናም በሰዎች ችግር እንቀልዳለን እንዲሁም የሰዎችን ችግር የኛ መሸጋገሪያ ድልድይ እናደርገዋለን፡፡

Stolen