Get Mystery Box with random crypto!

የገበሬው ደብዳቤ እጅግ በእድሜ የገፋ ብቻውን የሚኖር ጣሊያናዊ ገበሬ አባት በእስር ቤት ለ | መልካምነት ለራስ ነው!!!🌹🌹🌹

የገበሬው ደብዳቤ

እጅግ በእድሜ የገፋ ብቻውን የሚኖር ጣሊያናዊ ገበሬ አባት በእስር ቤት ለሚገኘው ብቸኛ ልጃቸው ደብዳቤ ይፅፋል::
'' ልጄ ያው በዚህ አመት ድንችና ቲማቲም መትከል አልችልም ምክንያቱም ማሳውን የማረስ አቅሙ ስለሌለኝ አንተ ግን እዚህ ሆነህ ቢሆን ኑሮ ልትረዳኝ እንደምንችል አውቃለሁ።''
ብሎ ፃፈለት

ልጅም ለአባቱ ሲመልስ:-'' አባቴ ሆይ ማሳውን ለማረስ ፈፅሞ እንዳታስብ ምክንያቱም የሰረቅኩትን ገንዘብ እዛ ስፍራ ቀብሬዋለሁ እና!'' በማለት መለሰለት።
ታዲያ በነጋታው የእስር ቤቱ አለቃና ፓሊሶች ልጅና አባት የሚመላለሱትን ደብዳቤ ቀድመው አንብበው ነበርና በጠዋት ተነስተው ወደ ስፍራው በማቅናት ገንዘቡን ለማግኘት ከዳር እስከ ዳር ማሳውን ቆፈሩት ነገር ግን ምንም አይነት ነገር ሊያገኙ አልቻሉም።
ቀጣይ ቀንም ልጅ ለአባቱ ደብዳቤ ፃፈ:-'' አባቴ አሁን ቲማቲም እና ድንቹን መዝራት ትችላለህ እዚህ ሆኜ ላደርግልህ የምችለው ትልቁ ነገር ይህንን ነወ።''
አባትም መለሰ:-'' ልጄ ሆይ በእርግጥም ብርቱ መሆንህን አውቃለሁ እስር ቤት ሁነህ እንኳን ለኔ ፓሊሶችን ታዛለህ። የእስር ቤቱ አለቃና ጀሌዎች አካፋና ዶማ ይዘው ማሳውን ሲቆፍሩ በማየቴ ተገርሜአለሁ የመህር ጊዜ ሲደርስ ምርቱን ለመሰብሰብ ስፈልግ ደሞ እልክልሀለሁ።'

ሰዎች ሁኔታዎች አካልህን ሊያስሩት ይችላሉ ነገር ግን አዕምሮህን ፈፅሞ አያስሩትም።