Get Mystery Box with random crypto!

...ከስራ ገብቼ እንደተለመደው ከልጄ ከዮአኪን ጋር በቲቪ ሪሞት እንጣላለን ቲቪውን የገዛውት እኔ | መልካምነት ለራስ ነው!!!🌹🌹🌹

...ከስራ ገብቼ እንደተለመደው ከልጄ ከዮአኪን ጋር በቲቪ ሪሞት እንጣላለን
ቲቪውን የገዛውት እኔ፣
Netflix የምከፍለው እኔ፣
IPTV የምከፍለው እኔ፣
Wifi የምከፍለው እኔ፣
ሪሞት ካልያዝኩ ብሎ እዬዬ የሚለው ግን እሱ ነው
ድንገት ቀና ስል ባለቤቴ ሁኔታችንን እያየች ትስቃለች፣ አንድም እስዋን ፈርቼ ሁለትም የእሱን ለቅሶ ላለመስማት ስል ለቀቅኩለት።

ወዲያው ባለቤቴ የሆነ ነገር ያስታወሰች ይመስል ፈገግ ብላ
"...ፍቅር.." አለችኝ
"..ወዬ.. "አልኳት ለምቦጬን እንደጣልኩ... ዮአኪን የሳንቾን ዘፈን ከፍቶ ይሸከሽከዋል ....ነፍሱን አያውቅም
"Valentine day እኮ" ደረሰ :አለችኝ
ኡፍፍፍፍፍፍ ኤጭጭጭጭ አሁንስ ምርር ያለኝ ነገር ይሄ 'ደረሰ' የሚለው ቃል.... የታባቴ ልግባ እሱን የማልሰማበት
'ፍቅር ቤት ኪራይ ደረሰ'...
'ውድ የሞግዚትዋ ደሞዝ ደረሰ'...
'ማሬ የመብራት ክፍያ ደረሰ'....
'ሃን የwifi ክፍያ ደረሰ'...
እረ ኡኡኡኡ የት ልግባ ጨለልኩ
ድሮ እኮ ባሻዬ 'አዳም ረታ አዲስ መጽሀፍ ደረሰ፣ ደራሲ አለማየሁ ገላጋይ አዲስ መጽሀፍ ደረሰ' .....ነበር የምባለው ለጉድ ይገዛል፣ ለጉድ ይነበባል።
አሁን የማንበብ ጥማቴን የምወጣው ለልጄ በሚገዛው የቆርቆሮ ወተት ላይ የተጻፈውን ingriedents ምናምን በማንበብ ነው ።

"ምነው ዝም አልክ?" አለችኝ
"እእእእእ..." አልኩ እንደ መባነን ብዬ
"ቫለንታይን ደረሰ እኮ ነው የምልህ... ምንድን ነው ስጦታ የምሰጠኝ ?" አለች
"ምንንንን ???" አልኩ እንደ መቆጣት ብዬ
"እንዴ ምነው ፍቅር ስጦታ እኮ ነው ያልኩህ?"
"እኔ ስንት አወጣለው...? አልኳት
"እንዴ ውድ ተወው በቃ ይቅር"
"ንገሪኝ ስንት አወጣለው... ሺ ፣ ሚሊዮን ቢሊዮን ወይስ ምንም...?"
"እረ ፍቅር ተው... እንዴ ...አንተ እኮ ማለት ለእኔ ሂወቴ ነህ፣ በምንም የማትተመን መለኪያ የሌለህ፣ ከፈጣሪ የተሰጠኽኝ ውድ ስጦታዬ እኮ ነህ!!" እምባዋ መጣ ሁልጊዜ ስለ እኔ ስታወራ እምባዋ ይቀድማታል
"ታዲያ ፈጣሪ እኔን የመሰለ ስጦታ ሰቶሽ ከእንደገና ከእኔ ሌላ ስጦታ መጠበቅ ፈጣሪን ማስከፋትስ አይሆንም ?? በሰጠኽኝ ስጦታ አልተደሰትኩም ማለት አይሆንም?? እንደው የፈጣሪን አይን መውጋትስ አያስመስልም?
ከፈጣሪ የተሰጠን ስጦታ ገሸሽ አድርጎ ነገ አፈር እና ትቢያ ለሚሆን ስጦታ እንዲህ መሆን ልክ ነው?" አልኩ በቁጣ
"እረ ፍቅር እኔ እንደዛ አላሰብኩም ነበር ይቅርታ አድርግልኝ" ብላ ስቅስቅ ብላ አለቀሰች
" እኔን አይደለም ፈጣሪን ነው ያስከፋሽው ነገ የንስሃ አባታችን ጋር ሄደን ንስሃ ትገቢያለሽ.."
"እሺ ፍቅር..."

ክበር ተመስገን ፈጣሪ እንደው ምን ይሳንሃል ከጉድ አወጣኸኝ valentine dayን እንዲህ አሳመንኩዋት (አሳምነው ይልሃል ይሄ ነው ስምን መልአክ ያወጣዋል ማለትስ ይሄ አይደል)

ደሞ ልደትዋም እየደረሰ ነው ልዘገጃጅ ፣
ለማክበር አይደለም ለማሳመን