Get Mystery Box with random crypto!

' እማዬ አንቺን ማሳፈር ስለማልፈልግ ጠፋሁ በጣም ነው የምወድሽ!በህይወትሽ ደስተኛ ሁኚ ' - ልጅ | መልካምነት ለራስ ነው!!!🌹🌹🌹

" እማዬ አንቺን ማሳፈር ስለማልፈልግ ጠፋሁ
በጣም ነው የምወድሽ!በህይወትሽ ደስተኛ ሁኚ " - ልጅ

" እባካችሁ ብቸኛ ልጄን እንዳላጣው አፋልጉኝ " - እናት

#ሼር በማድረግ እንፈልገው

ይህ የ13 ዓመት የ7ተኛ ክፍል ተማሪ ህፃን አቢኔዘር #ታደሰ ይባላል! ትላንት አርብ የካቲት4 እንደተለመደው አዲሱ ገበያ የሚገኘው ብርሀነ ህሊና ት/ቤት ይሄዳል።

የሂሳብ ትምህርት መምህሩ ደግሞ ወደ ክፍል ሲገባ አቢኔዘርን ጠርቶ "ውጤትህ ዝቅ ያለ ስለሆነ 7ተኛ ክፍልን መድገምህ አይቀርም" ይለዋል።

የተደናገጠው ተማሪ አቢኔ ወደ ቤቱ 10 ሰዓት አካባቢ ይገባና ዩኒፎርሙን ቀይሮ ከላይ ሸሚዝ ለብሶ ፎጣ በነጭ ፌስታል ይዞ ለሚወዳት እናቱም ይህን ደብዳቤ ፅፎ ጠፍቷል ቤተሰብ ሁሉም ተረብሿል።

ህፃኑ የፃፈው ደብዳቤ እንዲህ ይላል ፦

" እማዬ በጣም ነው የምወድሽ! ዛሬ እንደሚያስወድቁኝ ነገሩኝ! ስለዚህ አንቺን ማሳፈር አልፈልግም! ስለዚህ ነው የጠፋሁት። በተደጋጋሚ ወላጅ አምጣ ከተባልክ ታሳፍረኛለህ ስትይኝ ነበር!ስለዚህ ጠፋሁኝ! በጣም ነው የምወድሽ! በህይወትሽ ደስተኛ ሁኚ እሺ! በጣም እወድሻለሁ!አባቴንም ቻው በይልኝ እሺ እማዬ እወድሻለሁ ቻው love you mom "

ተረባርበን #SHARE_ሼር በማድረግ የእናቱን እንባ እንብስለት።

"ለመልካም ስራ ረፍዶ አያውቅም"
#ባይሽ_ኮልፌ_በጎ_አድራጎት
0910501427-አባይነሽ ነጋ
0943567813-ፀሀይነህ ሙሉ

@tikvahethmagazine