Get Mystery Box with random crypto!

የምህረት መላክ በሲና በረሃ ያወረደዉ መና የእስራኤል መሪ በአምደ ደመና የመላክት አለቃ ሚካኤል | የአካባቢ ወጣቶች መዝሙራት

የምህረት መላክ

በሲና በረሃ ያወረደዉ መና
የእስራኤል መሪ በአምደ ደመና
የመላክት አለቃ ሚካኤል ነዉና

የምህረት መላክ ቅ/ሚካኤል /2/
ፈጥኖ ይደርሳል ያማልደናል
በስጋም በነብስ ይታደገናል/2/

አዝ.........
ዳንኤልን ከአናብስት ባህራንን ከሞት
ቅድስት አፎምያን ከሰይጣን ያዳንካት
እኛንም አድነን መለአከ ምህረት
አዝ.........
ክብሩ ታላቅ ነዉ ድንቅ ነዉ ስሙ
ማን እንደ እግዚያብሔር መላከ ምክሩ
ቅዱስ ሚካኤል ድንቅ ነው ታምሩ
አዝ......
ተራዳይነቱ መፅሐፍ መስክረዋል
ስለ ህዝብ ልጆች ሚካኤል ይቆማል
ምህረት የሚያሰጥ ኪዳን ተቀብሏል
አዝ......
በመታሰቢያዉ ቀን ይነበብ ድርሳኑ
ዝክሩን እናዘክር ይከበር በአሉ
ሚካኤል ያድናል ምልጃዉ ቃልኪዳኑ

https://t.me/maheberat