Get Mystery Box with random crypto!

ታላቅ መንፈሳዊ የንግስ ጉዞ በስመአብ ወወልድ ወመንፈስ ቅዱስ አሀዱ አምላክ አሜን እንኳን ከዘመ | የአካባቢ ወጣቶች መዝሙራት

ታላቅ መንፈሳዊ የንግስ ጉዞ

በስመአብ ወወልድ ወመንፈስ ቅዱስ አሀዱ አምላክ አሜን

እንኳን ከዘመነ ማርቆስ ወደ ዘመነ ሉቃስ በሰላምና በጤና አሸጋገራችሁ እያልን እንደተለመደው ማህበራችን ፈለገ እንድሪል መንፈሳዊ የጉዞ ማህበር በአይነቱ ልዩ የሆነ የአዳር ጉዞ ወደ ታላቁ የጅሩ አርሴማ ገዳም አዘጋጅቶ ይጠብቆታል።

በጉዟችን ላይ የምንጎበኛቸው ቦታዎች፦

አቡነ ቀውስጦስ ገዳም (አፈራቸው 40 ቀን ያልሞላው መቃብር ላይ ቢነሰነስ ሲዖልን አያይም)
ጨለሚት ቅዱስ ጊዮርጊስ ቤ/ክ (ፀበል ቦታው ከዓመት ዓመት ፀሀይ ስለማያገኝ ነው ስያሜው የተሰጠው)
ሞቶሎሚ ቅዱስ ሚካኤል እና አቡነ ተክለሃይማኖት ቤ/ክ (አቡነ ተክለሀይማኖት በንብ ቀፎ የተጣሉበትና ቅዱስ ሚካኤል በክንፎቹ አቅፎ ያዳነበት ቦታ)
ስለቦታው በጥቂቱ

ቦታው ላይም የቅድስት አርሴማ የሚጠጣ የጡቷ ፀበል (ጡት ከሚመስሉ አለቶች መሀል የሚፈልቅ) ያለ ሲሆን ሲጠጣም ወተት ወተት የሚል ቃና አለው
የቅድስት አርሴማ ፀበል (ይኽኛው የመጠመቂያ ሲሆን መነሻው የማይታወቅ ከአመት አመት የማይቀንስ ፀበል ነው የምታጠምቀውም በቀስተ ዳመና ነው)
የሚጠጣ የቅድስት አርሴማ ፀበል (የጡቷን ፀበል መጠጣት የሚችሉት ቡና የማይጠጡ ወይም ከዛ በዃላ ላይጠጡ ቃል የሚገቡ ሰዎች ስለሆኑ ቡና ለሚጠጡ ሰዎች የተዘጋጀ)
የአቡነ አረጋዊ ፀበል
የኪዳነምህረት ፀበል

እንዲሁም ቦታው ላይ ለየት ያለ ድንጋይ የሚገኝ ሲሆን ሲሰበርም የዘንባባ፣ፅዋ እና የጡት ምስል ታትሞበት ይገኛል።

እነዚህና ሌሎች አስደናቂ ነገሮች የሚገኙበትን የጅሩን ቅድስት አርሴማን ገዳም ይጎበኙ ዘንድ ጋብዘነዎታል።


የጉዞ ቦታ የጅሩ ደብረ ልዕልና ቅድስት አርሴማ

የጉዞ ቀን መስከረም 28_29

የጉዞ ዋጋ 450 መስተንግዶን ሳይጨምር

የጉዞ መነሻ ቦታ ሸጎሌ ሩፋኤል፣ ዩሀንስ ማርያም፣ ጊዮርጊስ፣ ሰሜን ማዘጋጃ፣ አዲሱ ገበያ፣ ድልበር፣ ሚዛን፣ ሱሉልታ

የመነሻ ሰዓት ከለሊቱ 11:30

ማሳሰቢያ
የጉዞ ቦታ የምንይዘው ቢያንስ ግማሽ ክፍያ ሲከፍሉ ብቻ ይሆናል።
ለክፍያ 1000454269237
ናትናኤል አበባው
መጠቀም ይችላሉ። ወይም ይደውሉልን።
ምንጣፍ፣ ስሊፒንግ ባግ ፣ጋቢ ፣ለአዳር የሚሆኑ ነገሮች እንዳይረሱ

ለገጠሯ ቤተክርስቲያን የሚላክ 10 ጧፍ ግዴታ ነው

ምዝገባ ተጀምሯል
ለበለጠ መረጃም ሆነ ለምዝገባ መረጃ
@Natnael1201
+251901925758 ናትናኤል

ያሉን ቦታዎች ውስን ስለሆኑ ፈጥነው ይመዝገቡ።
ለጓደኞቻችሁ #share በማድረግ እንዲተባበሩን በአምላከ ቅድስት አርሴማ ስም እንጠይቃለን።