Get Mystery Box with random crypto!

እንባዋን ከልላ ሳቄን ምታጎላ መንገዴን አስታዋሽ መካሪዬ እንዳልዋሽ! እሷ ውቧ አይነ ’ርግቧ። | Bilal Media & Communication

እንባዋን ከልላ
ሳቄን ምታጎላ
መንገዴን አስታዋሽ
መካሪዬ እንዳልዋሽ!
እሷ ውቧ
አይነ ’ርግቧ።

ሳልደግፋት ካክራ ሆና
ፀንታ የኖረች ተፈትና
ቃል ቆጥባ የሰከነች
ስትገፋ የጀገነች
እሷ ፅኑ ባለ ልቧ
አይነ ’ርግቧ።

አርማ ክብሯ
ንግስ ድንበሯ
መታወቅያ ምልክቷ
መሰተሯ ጥልቅ ውበቷ
እንኳን ገላ ሲወርድ ላቧ
ሀያዕ አለው ያ’ይነ ’ርግቧ።

ዘመናይት በከፍታ
ሽሙንሙን ነች በዝምታ
ክፍት ሲላት አላት ኸሊል
ሽሽት ውሽቅ ወደ ጀሊል።
ሰናይ ሰብር ሰርክ ቀለቧ
አብሪዋ ጌጥ አይነ ’ርግቧ።
[ አብዱልሀኪም ሰፋ ]
:
@Venuee13
@Venuee13