Get Mystery Box with random crypto!

(( « ከናንተ በስተፊት የነበሩ ሰዎችን መንገድ ስንዝር በስንዝር ክንድ በክንድ ትከተላላችሁ ! ' | Bilal Media & Communication

(( « ከናንተ በስተፊት የነበሩ ሰዎችን መንገድ ስንዝር በስንዝር ክንድ በክንድ ትከተላላችሁ !
"ዳባ" (የምትባለው እንሰሳ) ጉርጓድ ውስጥ ቢገቡ እንኳን ተክትላቹ (ትገባላችሁ " እኛም ( እንዲህ በማለት) ጠየቅናቸው። " አንቱ የአላህ መልዕክተኛ ሆይ ! የሁዳና ነሳራን ማለቶት ነውን ?! " "ታዲያ ምንን ነው ? ( እነሱን ቢሆን እንጂ ) » ))

ከሃዲያንን የመከተላችንና የመውደዳችን ታማኝነት በመልዕክተኛው አንደበት በዚህ ደረጃ ነው የተገለፀው !!!

አዎ ! ስሜት አሸንፎን በመታወራችን የተነሳ መልካም አስከታይ ሳናጣ ... መጥፎ ተከታይ ሆነን ቀራን !!! አዎ ክፉዎች እየመሩን ውስጥ ሊከቱን እያሮጡን ነው ደጋጎቹ ቀደምቶች ደግሞ የውለታቸውን ክፍያ በትዝብት ከኛ እየተጠባበቁ ነው። « ወይ ! የኛ ነገር ... ውለታ በዪ ሆነን መቅረታችን ... ያሳዝናል !!! ምን ይሆን ፍፃሜያችን ??? »

የቂያማ ዕለት አምላካችን አላህ ዘንድ እውነቱን ሳንጨምር ሳንቀንስ "ዒድ" ብለን አክብረን አሳይተን አደራችንን ተወጥተናል ሲሉ... አደራውን ቆረጣጥመን የበላነው እኛ መልሳችን ምን ይሆን ???

قال شيخ الإسلام ابن تيمية رحمه الله : ( وأما اتخاذ موسم غير المواسم الشرعية كبعض ليالي شهر ربيع الأول التي يقال : إنها ليلة المولد , أو بعض ليالي رجب , أو ثامن عشر ذي الحجة , أو أول جمعة من رجب , أو ثامن من شوال الذي يسميه الجهَّال عيد الأبرار : فإنها من البدع التي لم يستحبها السلف , ولم يفعلوها. والله سبحانه وتعالى أعلم). ا.هـ. مجموع الفتوى لشيخ الإسلام ابن تيمية (25/298).

አላህ ይዘንለትና ሸይኸል ኢስላም ኢብን ተሚያ እንዲህ ነበር ያለው ፦

« ሸሪዓው ካደረገው የክብረ-በዓል ውጪ መያዝን ከሆነ ... ልክ ከፊል የረቢዓል-አወል ወር ሌሊቶችንና የነብዩ (ሰለላሁ ዓለይሂ ወሰለም)
የልደት ቀን በማለት ማክበር ፤ ከፊል የ"ረጀብ" ወር ሌሊቶችን ፥
የዙል-ሒጃ 18ኛውን ቀን ፥ ከ"ረጀብ" ወር የመጀመሪያውን "ጁምዓ"ና እነዚያ መሀይባን የሆኑ ሰዎች ደሞ "ዒዱል አብራራ"
( የምርጦች ዒድ) በማለት የሰየሙት የሆነው ከ"ሸዋል"ወር 8ኛውን ቀን "ዒድ" አድርጎ ማክበር
ቀደምት ደጋግ ሰለፎች ያልወደዱትና ያልተገበሩት የሆነ "ቢድዓ" (አዲስ ፈጠራ) ነው !!! »

ጥራት የተገባውና ከፍ ያለው አላህ የበለጠውን ዐዋቂ ነው !!!

መጅሙዓ ፈታዋ (25/298)

ታዲያ ለምን አንመከርም ?? ስለምንስ አንገሰፅም ?! የኛ ባልሆነ ነገር መጌጥ እየፈለግን እውነተኛው ኢስላም ያወጀልንን የ"ዒድ" ገፅታ
እናበላሻለንን ?!

አዎ ! ኢስላም ያወጀልን ዓመታዊ ባህላችን (ሁለት ነው !!!)

« ومما أحدث الناس اليوم بدعة عيد الأم، عيد فلان، عيد فلانة، تشبه بأعداء الله، هذه الأعياد تشبه بالنصارى واليهود، هم أهل الأعياد، وليس لنا إلا عيدان نحتفل بهما: عيد الأضحى، وعيد الفطر، وليس لنا أن نحدث احتفالات بأعياد أخرى،...»

(دروس و محاضرات)

(التعليقات على ندوات الجامع الكبير)

الإمام ابن باز رحمه الله

  « በአሁን ጊዜ ሰዎች የፈጠሩት ከሆነው አዲስ ነገር ውስጥ የ" እናት ዒድ" ፥ የእከሌ "ዒድ" ፥ የእከሊት "ዒድ" ፥ የሚባለው ነገር ሲሆን በአላህ ጠላቶች መመሳሰልም ነው

እነዚህን በዓላቶች (ማክበር) በነሳራና በየሁዳዎች መመሳሰል ነው !!! እነሱ የበዓላት ባልተቤቶች ናቸውና።

ለኛ ደሞ የምናከብራቸው የሆነው ሁለት ዒዶችን እንጂ ሌላ የለንም !!!

እነሱም ፦ "ዒድ አል-አድሓ"ና
"ዒድ አል-አፍጥር" ናቸው።

እኛ ሌላ ዒዶችን (በዓላቶችን) ለማክበር ስንል "ቢድዓ" መፍጠር የለብንም !!! ... »

(( ሰማሓቱ ሸይክ ኢማም ዐብዱላዚዝ ቢን ዐብደላህ ቢን ባዝ ))

በጣም የሚገርመኝ ነገር ...

መረጃ ያልመጣበት መሆኑ አንድ ነገር ሆኖ ሳለ ካፊሮችን መመሳሰልና መፎካከር ካልሆነ ለምን ከ"ሸዋል" ፆም ውጪ የሚፆሙትን እንደሁም አጅር በማስገኘት ወይም በጊዜው በላጭነት ወይም ወንጀልን በማሳበስ ወይም ከረመዳን ፆም ቀጥሎ ባለው ደረጃ ... ከ6ስቱ የሸዋል ፆም የሚበልጡ ሱና ፆሞች አሉና ለምን ዒድ አድርጎ ከመያዝ ተቆጠብን ?!!!

መልሱ ግልፅ ነው !!! የእውነት ዲናችንን እንገንዘብ !!! ከስሜት እንውጣ !!! በዕምነታችን አንፈር !!!

አላህ ሆይ ቀናውን መንገድ ምራን !!!

ወንድም እህቶች ለአላህ ብላቹ "ሼር" አርጉት !!!

https://t.me/amr_nahy1
https://t.me/amr_nahy1
https://t.me/amr_nahy1

… ኢስማኤል ወርቁ …