Get Mystery Box with random crypto!

የአብራሮች 'ዒድ'ና ኢስላም... بسم اللــــه الرحمـــن الرحيم. (( ' اتّ | Bilal Media & Communication

የአብራሮች "ዒድ"ና ኢስላም...

بسم اللــــه الرحمـــن الرحيم.

(( " اتَّبِعُوا مَا أُنزِلَ إِلَيْكُم مِّن رَّبِّكُمْ وَلَا تَتَّبِعُوا مِن دُونِهِ أَوْلِيَاءَ ۗ قَلِيلًا مَّا تَذَكَّرُونَ " ))

« ከጌታችሁ ወደ እናንተ የተወረደውን ተከተሉ፡፡ ከአላህም ሌላ ረዳቶችን አትከተሉ፡፡ ጥቂትን ብቻ ትገሰጻላችሁ፡፡ »

(( " وَاتَّبِعُوا أَحْسَنَ مَا أُنزِلَ إِلَيْكُم مِّن رَّبِّكُم مِّن قَبْلِ أَن يَأْتِيَكُمُ الْعَذَابُ بَغْتَةً وَأَنتُمْ لَا تَشْعُرُونَ " ))

« እናንተ የማታውቁ ስትኾኑም ቅጣቱ በድንገት ሳይመጣባችሁ በፊት ከጌታችሁ ወደናንተ የተወረደውን መልካሙን (መጽሐፍ) ተከተሉ፡፡ »

ከነዚህ የተቀደሱ የአላህ ንግግሮች የምንረዳው ከፈጣሪያችን አላህ እንዲሁም ከመልዕክተኛው ዘንድ የመጣውን ብቻ መከተል እንዳለብን ነው።

(( ... ما رواه أبو داود في سننه عن أنس رضي الله عنه قال قدم رسول الله صلى الله عليه وسلم المدينة ولهم يومان يلعبون فيهما فقال: "ما هذان اليومان؟ قالوا: كنا نلعب فيهما في الجاهلية ، فقال رسول إن الله قد أبدلكم بهما خيراً منهما يوم الأضحى ويوم الفطر " ... ))

ሱነን ውስጥ አቡ ዳውድ እንደዘገበውና አነስ ቢን ማሊክ እንዳወራው ፦

(( « ነብዩ (ሰለላሁ ዐለይሂ ወሰለም) ወደ "መዲና" የሄዱ ጊዜ (ለመዲና) ሰዎች ሁለት የሚጫወቱባቸው የሆነ ዕለቶች (ክብረ-በዓል) ነበራቸው። እሳቸውም እንዲህ አሉ ፦
« ምንድናቸው እነዚህ ሁለት ዕለቶች ? » እነሱም እንዲህ አሏቸው ፦ « እኛ በጃሂሊያ ጊዜ (በነዚህ ቀናቶች) ውስጥ የምንጫወትበት ነበር። » ረሱልም
(ሰለላሁ ዐለይሂ ወሰለም) እንዲህ አሉ ፦ « አላህ በእርግጥም ከነዚህ ቀናቶች ይልቅ የተሻለን የ"ዒድ አል-አፍጥርና የዒድ አል-አድሓን ቀናቶቾ ቀየረላቹ። » ))

ከዚህ ሐዲስ እንደምንረዳው
ከነዚህ ሁለት ዒዶች ውጪ ሌላ ቢኖር ኖሮ ነብዩ (ሰለላሁ ዐለይሂ ወሰለም) ለባልደረቦቻቸውና ለህዝባቸው ባሳወቁ እንደነበረ ነበር !!!

ስለዚህ ከዚህ በመነሳት ከነዚህ (2) ዒዶች (በዓላት) ውጪ
ሌላ ተጨማሪ "ዒድ" በዓል ማክበር አዲስ ፈጠራ "ቢድዓ" ይሆናል ማለት ነው

ሌላውም የመልዕክተኛው ንግግር የሚያመላክተው ይህንኑ ነው ፦

(( " وقد قال رسول الله صلى الله عليه وسلم: "من أحدث في أمرنا هذا ما ليس منه فهو رد " أخرجه مسلم في صحيحه، " ))

(( " በዚህ ጉዳያችን (ዕምነታችን)
ውስጥ ከሱ ያልሆነን አዲስ ነገርን የፈጠረና የሰራ የሆነ ሰው ስራው ተመላሽ ይሆንበታል !!! " ))

(ሰሒሕ ሙስሊም)

ታዲያ ሊሆን የሚገባው እውናታ ይህ ሆኖ ሳለ እኛ በተለይም በዚህ ዘመን ላይ ያለን ሙስሊሞች እጅግ አስደንጋጭ በሆነ ሁኔታ ከአላህ በመቀጠልም ከመልዕክተኛው ዘንድ በመጣልን ነገር ከመብቃቃት ይልቅ የተሟላውን እስልምና ጎዶሎ አርጎ ሊያሳይ በሚችል መልኩ አዳዲስ... በደጋግ ቀደምቶቻችን የማይታወቁ ነገሮችን በማምጣትና የዚንጀሮ ቆንጆ ዓይነት በማስመሰል ተፈጥሮአዊ የሆነውን እስልምና ጥላሸት ቀብቶ ማግማማቱን እየተካነው ነው ግን ለምን ???
ባለውለታው እስልምና አይፋረደንም ይሆን ???

ግን ለምን ?! ለእያንዳንዱ ድርጊታችን ከጌታችን አላህ ከወረደልን ድንጋጌ ይልቅ ከሀዲያኖችን ሞዴል ማድረጋችን ???

ውርደትን በገዛ እጃችን በመፈለጋችንም አይደለም ??!

ተጠያቂው ማነው ???

አዎ ! ተጠያቂውማ እምቢተኛና አጥፊው ነው

እኔ ግን ከተጠያቂነት ለመዳን ስል እቺን ተግሳጽ አድርሼሃለሁና አድርሱልኝ ብያለሁ !!! አደራ !!! አማና !!!

ታላቁ " ኢማም ኢብን ባዝ " ከተጠያቂነት ለመዳን ሲሉ የሰጡትን ዕውቀታዊና ጥበበኛ ግሳፄያቸውንና አደራቸውን እንዲህ በማለት አድርሰውም ነበር።

فالذين يحدثون أعيادًا ما أنزل الله بها من سلطان إنما كانوا بهذا في الحقيقة معارضين ومشاقين لما شرعه الله ورسوله، ومتشبهين بأعداء الله من اليهود والنصارى فيما أحدثوا من الأعياد الباطلة التي لا أساس لها في شرعنا، بل غيروا وبدلوا وأحدثوا، فغضب الله عليهم سبحانه وتعالى، فعلينا أن نحذر أن يغضب الله علينا كما غضب عليهم في الإحداث والبدع والمعاصي والمخالفات.

ونسأل الله للجميع العافية والسلامة، ولا حول ولا قوة إلا بالله.

(دروس و محاضرات)

(التعليقات على ندوات الجامع الكبير)

الشيخ الإمام ابن باز رحمه الله

« እነዚያ አላህ ከመረጃ ምንም ያላወረደበት የሆነውን "ዒድ " የሚፈጥሩ የሆኑ ሰዎች በትክክልም እነኚህ ሰዎች አላህና መልዕክተኛው ከደነገጉት ድንጋጌ አፈንጋጮችና ሰንጣቂዎች ናቸው እንዲሁም ከአላህ ጠላቶች የሁዳና ነሳራ ጋርም እየተመሳሰሉም ነው !!!

እነሱ በሸሪዓችን መሰረት የሌላቸውን ውድቅ የሆኑ ዒዶችን በማስገኘት (ከካዲያኖች) ጋር ተመሳሰሉ። ቀየሩ ! ለወጡ ! ፈጠሩ ጥራት የተገባውና ከፍ ያለው አላህም ተቆጣባቸው !!!

(ታዲያ) አላህ በእነሱ ላይ በአዲስ ነገር ፥ በ"ቢድዓ" በወንጀልና በተቃርኖ እንደተቆጣባቸው ሁላ በኛም ላይ እንዳይቆጣብን ዘንዳ ልንጠነቀቅ ይገባል !!!

አላህ ለሁላችንም ጤናንና ሰላም መሆንን እንጠይቀዋለን !!!

« በአላህ ቢሆን እንጂ ዘዴ ብልሃትም ይሁን ኃይል የለም !!! »

(( ሰማሓቱ ሸይክ ኢማም ዐብዱላዚዝ ቢን ዐብደላህ ቢን ባዝ ))

ካፊሮች የ2 ወር ፆማቸውን ጨርሰው " ትንሳዔ" ይላሉ። ከዚያም በሳምንቱ ዳግማዊ " ትንሳዔ" ይሉና የሚያረጉትን ያረጋሉ

ለበዓላቸው ህግ ደንብና ስርዓትን የሚያበጅለት የሆነ መለኮታዊ ትዕዛዝ ያልመጣበትና መመሪያ የሌለው ስለሆነ ማንም እንደፈለገውና እንደተመቸው ተነስቶ ደስ ያለውን አፅንቶ ደስ ያላለውን ይሽራል እነሱ ጋር ...የፈለጉትን "ዲን" አርጎ መያዝ አያስጠይቅምም !!!

ታዲያ እኛጋስ ??? እኛጋማ ጥርጥር የለውም !!!
ምናልባት "ዳባ" የምትባለው እንሰሳ ምሳ የገባችበት ጉርጓድ ውስጥ ካልገባው ብሎ እነሱን የተከተላቸው ካልሆነ በስተቀር...
ያለድንጋጌና ያለመረጃ አምልኮት የሚባል ነገር እንደሚያስጠይቅ
ጠንቅቆ ያውቃል !!!...

فعن أبي سعيد الخدري أن رسول الله صلى الله عليه وسلم قال: ((لتتبعُنَّ سَنَنَ من كان قبلَكم، شبرًا بشبرٍ، وذراعًا بذراعٍ، حتى لو دخلوا جُحْرَ ضبٍّ تبعتُمُوهم))، قلنا: يا رسولَ اللهِ، اليهودُ والنصارى؟ قال: ((فمَنْ؟)) [البخاري: 7320].

አቢ ሰዒድ አል-ኹድሪይ ረሱል (ሰለላሁ ዐለይሂ ወሰለም) አሉ በማለት እንዲህ አለ ፦