Get Mystery Box with random crypto!

> > > > > > > (አብዱልሀኪም ሰፋ) : @Venuee13 @Venuee13 | Bilal Media & Communication

<< አንቱ ሰው እንዴት ያለ ፍቅር ነው ጊዜ የማያስረጀው? >>
<< የኔ ልጅ ካለመጠን ከፍ የማታደርገው፣ ከወሰኑ የማታሳንሰው፣ ሀቁን የምትጠብቅለት ፍቅር በጊዜ ውስጥ ፈገግታው ይጨምራል። ፍቅር አደራ የመጠባበቅ ቃል ኪዳን ነው። ሀቁን ለባለ ሀቁ ስታደርስ ሀቅህ አይጓደልም። >>
<< ፍቅሮን እንደምን ጠበቁ? >>
<< ፍቅር የሚቸረውን የፍቅር ባለቤትን ሀቅ ለመጠበቅ ሞከረን እንጂ የፍቅር ምንጩን እየዘነጋን ፍቅራችንን ለመጠበቅ አልሞከርንም። ፍቅራቸውን ብቻ ለመጠበቅ የሚታገሉቱ የሚስቱት ይበዛል። የኔ ልጅ የፍቅር ምንጩን ሀቅ ጠብቅ ፍቅርህ ንፁህ ይሆናል። >>
<< አንቱ ሰው እወዶታለሁ! >>
<< የፍቅር ምንጩን ከማጣት ይጠብቅህ! >>
<< አሚን! >>
(አብዱልሀኪም ሰፋ)
:
@Venuee13
@Venuee13