Get Mystery Box with random crypto!

ቢያንስ ለመስጂዶች ክብር ይኑረን እንጂ ~ መስጂዶች የተከበሩ የአላህ ቤቶች ናቸው። ለዒባዳ የተገነ | Bilal Media & Communication

ቢያንስ ለመስጂዶች ክብር ይኑረን እንጂ
~
መስጂዶች የተከበሩ የአላህ ቤቶች ናቸው። ለዒባዳ የተገነቡ ክቡር ስፍራዎችን የመቃሚያ ቦታ ማድረግ የሚሰቀጥጥ ተግባር ነው። ከጥፋት መታቀብ ቢያቅተን ቢያንስ ለጥፋት ቦታ ልንመርጥ ይገባል።
ወገናችንን ከዚህ መርዝ ቅጠል ይገላግለው። ለዚህ ሁሉ ህዝብ በዚህ ቅጠል ሱስ መለከፍ ቀዳሚ ተጠያቂዎች ዱዓቶችና መሻይኾች ናቸው። ለወገኑ ከልቡ የሚቆረቆር እውነተኛ አስተማሪ ማለት መሬት ላይ ባለው ተጨባጭ ተሸንፎ ህዝብን የሚያስደስት ፈትዋ የሚሰጥ ሳይሆን የአላህ ፍራቻን አስቀድሞ ያለውን መራር እውነታ የሚጋፈጥ ነው። የወገኑ ጉዳት የሚያመው ሁሉ! በሚችለው መድረክ ሁሉ ከዚህ መርዛማ ቅጠል ሰዎችን ሊያስጠነቅቅ ይገባል። በዚህ ቅጠል የተለከፉ ወገኖችን ከሱስ ማውጣት ቢያቅተን እንኳ ቢያንስ ልጆቻቸውን በሚጠብቁበት መልኩ በቂ ግንዛቤ እንዲጨብጡ ብናደርግ ቀላል ስኬት አይደለም።
~
የቴሌግራም ቻናል፦
https://t.me/IbnuMunewor