Get Mystery Box with random crypto!

ሔንሪ መክው የተባለ የክርስትና እምነት ተከታይ ምዕራባዊ ፀሀፊ ስለ ኒቃብ እንዲህ ይለናል፦ Mah | Bilal Media & Communication

ሔንሪ መክው የተባለ የክርስትና እምነት ተከታይ ምዕራባዊ ፀሀፊ ስለ ኒቃብ እንዲህ ይለናል፦

Mahi Mahisho

"በቢሮዬ ግድግዳ ላይ ሁለት የተሰቀሉ ምስሎች አሉ። አንደኛዋ ኒቃብ የለበሰች የሙስሊም ሴት ፎቶና ከጎኗ ደግሞ እራፊ ጨርቅ ላይዋ ላይ ጣል ያረገች እርቃኗን ለቁንጅና ውድድር የምትሳተፍ አሜሪካዊት።

የመጀመሪያዋ ከዓለም ሁሉ ገላዋን የደበቀች ሽፍን ውድ ሴት ሁለተኛዋ ደግሞ ለዓለም ገላዋን ባደባባይ የምታሳይ ርካሽ ሴት!

በምዕራቡና በምስራቁ ዓለም የሚደረገው ጦርነት በዋናነት ያነጣጠረው ዐረቦችም ሆኑ ሙስሊሞች ከሀይማኖታቸውና ከመልካም ባህላቸው ርቀው እርቃን እንዲወጡና ኒቃብን በአጭር ቀሚስ እንዲተኩ ነው።
ስለሆነም እኔም ኒቃብ በሀይማኖቴ ውስጥ ካለው ቦታ በመነሳት ከሱ እከላከላለሁ። ሴት ልጅ ለባሏ እና ለቤተሰቧ ያላትን ክብር ማሳያ ናት። የነርሱ ብቻ እንደሆነች ማመላከቻ ነው። ውድ ዕቃ ናትና ማንም እንዳሻው ሊያያት አትፈቅድም።

እርቃኗን ሆና ለሚሊዮኖች ገላዋን በቴሌቪዥን የምታሳየው የአሜሪካዋ የቁንጅና ንግስት ንብረትነቷ ለሁሉም ነውና የኔ ናት ብሎ የሚከራከር የለም። ሁሉም እንዳሻው ያያታልና"

የምዕራቧ ሴት የክብሯን መገለጫ የሆነውን ሐያዋንና ጥብቅናዋን አጥታለችና ምንም የሚስብ ነገር የላትም። ስሜትም ፍቅር አትሰጥም። አስቀድማ ፍቅርን ጨርሳለችና ለፍቅርም የታደለች አይደለችም።
በምዕራቡ ዓለም ያለች እንስት የወንዳወድነትን ባህሪ በመላበሷ ሚስትም ሆነ እናት የመሆን ሞራልም ሆነ አቅም የላትም። እንስሳዊ የስሜት ፍላጎትን ከማርካት ውጪ ለፍቅርም ሆነ ልጅን ለማፍራት ምቹ አይደለችም"

በርግጥ በራስ ላይ ከመመስከር የበለጠ ሌላ ምስክርነት አያሻም። አላህ ኒቃባችሁ ላይ ያፅናችሁ።

@yesheh_kalidrashid_daewawoch
@yesheh_kalidrashid_daewawoch