Get Mystery Box with random crypto!

ወገኔ ሆይ! የሚቀድመውን አስቀድም ~ ሃይማኖታዊ ብሽሽቅ ውስጥ እየገባህ እምነትህን አታርክስ። አደ | Bilal Media & Communication

ወገኔ ሆይ! የሚቀድመውን አስቀድም
~
ሃይማኖታዊ ብሽሽቅ ውስጥ እየገባህ እምነትህን አታርክስ። አደባባይ እና ጎዳናዎችን በሰንደቅ የሚያሸበርቁ ሰዎችን አይተህ አንተም በፊናህ በየጎዳናው የጨረቃና ኮከብ ምልክት የያዙ የመብራት ጌጦችን በመትከል ላይ አትጠመድ። በየጎዳናውና በየመጠለያው የወደቁ ወገኖችን ከማሰብ ይልቅ የረባ ቁም ነገር ሳይኖረው በሚሊዮን የሚቆጠር ገንዘብ ለሚወጣበት የጎዳና ላይ ኢፍጣር የጋለ ፍላጎት የምናሳየው ታይታና ከሆኑ አካላት ጋር ያለን የፉክክር ስሜት ስለሚጎላ ነው። የሰው እጅ እየጠበቀ ያለውን ምስኪን ከማስፈጠር ይልቅ ሰፈር አቆራርጦ፣ ካሜራ ደቅኖ፣ ሳይቸግረው ጎዳና ላይ ተጠራርቶ ማፍጠሩ የበለጠ የሚያስደስተን የሆነ የጎደለን ነገር ስላለ ወይም የሆነ በሽታ ስለገባብን ነው። ሶላት፣ ሶደቃ፣ ፈጥራ፣ ኢስላማዊ አለባበስ፣ ... ወደ አላህ መቃረቢያ አምልኮታዊ ተግባራት እንጂ የመንደር መበሻሸቂያ አይደሉም። "ጠላት አይኑ እያየ ጆሮው እየሰማ ..." የሚለውን መዝሙር በ"ኢስላምኛ" አታዚም። ለፉክክር የሚወጣውን ገንዘብ በዚህ በከበረ ወር ልባቸው የተሰበረ ወገኖችህን ለማገዝ ብታውለው ብዙ ፋይዳ አለው። ሃሳቤን ልክ አንድ መጠለያ ውስጥ ያለ ወገንህ እንደሰጠው ትዝብት አድርገህ እየው።
=
የቴሌግራም ቻናል :-
t.me//IbnuMunewor