Get Mystery Box with random crypto!

እኚህ ናቸው ሰለፎቼ (1) ~ ዑቅባህ ብኑ ዐልቀማህ ረሒመሁላህ እንዲህ ይላሉ፡- “አርጣህ ብኑል | Bilal Media & Communication

እኚህ ናቸው ሰለፎቼ (1)
~
ዑቅባህ ብኑ ዐልቀማህ ረሒመሁላህ እንዲህ ይላሉ፡-

“አርጣህ ብኑል ሙንዚር ዘንድ ነበርኩ፡፡ በቦታው ከነበሩ ሰዎች አንዱ 'ከአህሉ ሱና ጋር አብሮ ስለሚቀመጥና ስለሚቀላቀል ነገር ግን ስለ ቢድዐ ሰዎች ሲወራ 'ተውን እንግዲህ ስማቸውን አታንሱ!' ስለሚል ሰው ምን ትላላችሁ?' ሲል ጠየቀ፡፡ አርጣህ የዚህን ጊዜ እንዲህ አለ፡-

'እሱ እራሱ ከነሱ (ከቢድዐ ሰዎች) ነው፡፡ እንዳይሸውዳችሁ!'
አርጣህ ይህን ማለቱ አላስደሰተኝምና ኢማም አውዛዒይ ዘንድ ሄድኩኝ፡፡ እሱ እንዲህ አይነት ነገር ሲደርሰው ገላጭ ነበር፡፡ (አርጣህ ያለውን ስነግረው) 'አርጣህ እውነት አለ፡፡ እውነታው እሱ ያለው ነው፡፡ ይሄ ግን ስማቸው እንዳይነሳ ነው የሚፈልገው፡፡ ስማቸው ካልተነሳ እንዴት ነው ሰዎችን ከነሱ የምታስጠነቅቀው?!' ”
[ታሪኹ ዲመሽቅ፡ 15/8]

አስተውሉ፡-
ይሄ የተባለው ስማቸው እንዳይነሳ ስለሚፈልገው ነው፡፡
- እራሱን ለነሱ ጠበቃ ያደረገውንስ ምን እንበለው?
- ቢድዐቸውንና ጥመታቸውን ስለሚያሚያሰራጨውስ ምን እንበል?

(ኢብኑ ሙነወር፣ ነሀሴ 03/2006)
=
የቴሌግራም ቻናል፡-
https://t.me/IbnuMunewor