Get Mystery Box with random crypto!

እነሆ ዳሩል አርቀም ሁለተኛ አመቱን አስቆጠረ...! ሆኖም ይህንን በማስመልከት የዳሩል አርቀም ጉ | Bilal Media & Communication

እነሆ ዳሩል አርቀም ሁለተኛ አመቱን አስቆጠረ...!

ሆኖም ይህንን በማስመልከት የዳሩል አርቀም ጉዞ በመድረክ ፕሮግራሞች በእለተ እሁድ ጥር 21 ከጠዋቱ 2፡30 ላይ ሁለተኛ አመቱን አሸብርቆ ለማለፍ አስቧል። ዳሩል አርቀም ከዚህ በፊት የተለያዩ ኸይር ተግባራት ላይ በተለይም ከአይታሞች ፈገግታ ፣ከእናቶች እቅፍ እና ከተቸገሩ ቤተሰቦች መቃናት ጋር የተለያየ ሚና ተጫውቷል። በፕሮራማችን ላይም የተለያዩ ተቋማትን ጋብዘናል ለምሳሌ ኑጁም፣ በጥበብ ቢ ፓዘቲቭ፣ ሰባት ፣ጀመዐቱል ኸይርያ፣ነጃሺ መድረሳ፣ ሀሊፍ ...ምን ተቋማት ብቻ የተለያዩ ድንቅ ኡስታዞችም አሉን እነማን አትሉም? ኡስታዝ አብዱልመጂድ ፣ኡስታዝ ሀሺም፣ሸህ ሙሀመድ አሚን ... አሰልጣኝ ፋንታሁን ሀሰን
ጋዜጠኛ ፉአድ ሙህዲንም ድምቀታችን ነው። ብቻ ምን አለፋቹ ሁሉም አለ ከእናንተ ሚጠበቀው መምጣት እና የበጎነት መንገዳቸውን መመልከት ነው።



ትኬቱን የት አገኛለሁ? ሲሉ እንዳያስቡ ጭምር ዳሩል አርቀም አስተማማኝ ቦታወች ላይ ትኬቱን እንድታገኙ አመቻችቷል።
ስለዚህ በፕሮግራማችን መታደም ለምትፈልጉ በሙሉ

በኮተቤ አከባቢ ለምትገኙ፦ መሳለሚያ ማሪያም ቤተ ‑ ክርስቲያን ፊትለፊት አለን ይላል..ለበለጠ መረጃ 0939963771 ማግኘት ይችላሉ።

እንዲሁም ፦ ሜክሲኮ ፣ፒያሳ ፣መካኒሳ፣ ሳር ቤት፣ መርካቶ ለምትገኙ +251 910600970 ላይ ደውለው ማግኘት ይችላሉ።

በተጨማሪም ፦ አባዶ ፣ አያት ፣ ጣፎ ለምትገኙ 0923980314 ላይ ደውለው ትኬቱን ማግኘት ይችላሉ።

እንዳያመልጦ!