2022-06-19 08:21:02
ፍቅር» ምን እንደሆነ ያውቁ ኖሯል መገን ፋቅር???
.
#እውነተኛ_ፍቅር_ማለት፦
☞ ነብዩ ﷺ ለባልደረባቸው ሰውባን ረዲየሏሁ ዐንሁ ምንድነው ፊትህን የቀየረው? ብለው
ሲጠይቁት «በሽታም ሆነ ህመምም የለብኝም፤ ግን አንቱን ሳላገኝ ስቀር ከባድ የሆነ
ብቸኝነት ይሰማኛል፤ አንቱን እስከማገኞዎ ድረስ» ማለቱ ነው።
.
#እውነተኛ_ፍቅር_ማለት፦
☞ አቡበከር አስ-ሲዲቅ ረዲየሏሁ ዐንሁ ከነብዩ ጋር በሂጅራ ጉዟቸው ወደ ዋሻ ከመግባታቸው በፊት
«ወሏሂ ካንቱ በፊት ካልገባው በስተቀር አትገቡም፣ የሆነ ነገር ቢኖር እንኳ ካንተ በፊት
እኔን ይጉዳኝ» ማለታቸው ነው።
.
#እውነተኛ_ፍቅር_ማለት፦
☞ ዐሊይ ኢብን አቢ-ጧሊብ ረዲየሏሁ ዐንሁ በነብዩ ﷺ ፋንታ በፍራሻቸው መተኛታቸው ነው፤
የመካ ሙሽሪኮች ነብዩን ﷺ ለመግደል መስማማታቸውና በዛ ፍራሽ ላይ ሊሞቱ
እንደሚችል እያወቁ መተኛታቸው ነው።
.
#እውነተኛ_ፍቅር_ማለት፦
☞ ቢላል አል-ሐበሺይ ረዲየሏሁ ዐንሁ ነብዩ ﷺሲሞቱ የነብዩ ﷺ ፍቅር መዲና
አላስቀምጥ ብሎት አዛን ማድተጉን መተዉና መዲናን ጥሎ መሄዱ ነው፤ ይህ ብቻም
ሳይሆን ነብዩ ﷺ በህልሙ መጥተውበት ምንድነው እንዲህ መጥፋት? ለምን
አትዘይረንም? ሲሉት ገና ሌሊቱ እንደነጋ የነብዩን ﷺ ቀብር ዚያራ ለማድረግ መጓዙ
ነው፤ ከዛም አዛን እንዲያደርግ ለምነውት ያን ጣፋጩን አዛን ሲያደርግ የመዲና ህዝብ
በሙሉ በእንባ መራጨቱ ነው። ነብዩ ﷺ ከሞቱ በኃላ እንጂ እንደዛ አይነት እልቅሻ
አልታየም ተብሎ በታሪክ ኢስኪፃፍ ድረስ።
.
#እውነተኛ_ፍቅር_ማለት፦
☞ ከበኒ ዲናር የሆነች ሴት ባሏ፣ አባቷና ወንድሟ ወደ «ኡሑድ» ዘመቻ ወጥተው ሳለ
ሙስሊሞች ከውግያው ሲመለሱ ሁሉም እንደሞቱ ሲነገራት «ነብዩ:ﷺ እንዴት ሆኑ?
ብላ መጠየቋ ነው፤ ከዛም እሳቸው አልሞቱም ሲሏት እሳቸውን ካላየው ብላ ነብዩን ﷺ ስታያቸው «ካንቱ በኃላ ያለ ሙሲባ ሁሉ ለኔ ገር ነው» ማለቷ ነው።
.
#እውነተኛ_ፍቅር_ማለት፦
☞ ዙበይር ረዲየሏሁ ዐንሁ የ15 አመት ወጣት ሆኖ የነብዩን ﷺ መገደል የውሸት ወሬ ሲሰማ
የመካ መንገዶች ላይ ሰይፉን እየጎተተ መውጣቱ ነው።
.
#እውነተኛ_ፍቅር_ማለት፦
☞ ረቢዐተ ኢብን ከዕብን ረዲየሏሁ ዐንዩ ነብዩ ﷺ ምንድነው ሓጃህ (ጉዳይህ) ሲሉት ካንቱ: ጋር
በጀነት ጓደኛ መሆን ነው ማለቱ ነው።
.
«አንድ ሰው ከወደደው ሰው ጋር በቂያማ ይቀሰቀሳል» ማለቶን እናውቃለን፤
#እኔም_አንቱ
የአሏህ መልዕክተኛ ሆይ! እንወዳችኃለሁ በአባቴ፣ በእናቴ፣ በቤተሰቦቼ፣ በንብረቴና
በነፍሴ ፊዳዕ ልሁንሎ አንቱ የአሏህ መልክተኛ ﷺ
https://t.me/+UQPW2AMcMophYThk
20 viewsفردوس, 05:21