Get Mystery Box with random crypto!

ሙሐመድ ነው! የአዛቡ! የጀሒሙ! መጋረጃው፣ ለጀነቱ! የጉዞ ስንቅ! መነገጃው፣ የካኢኑ መደራጃው፣ | 👳‍♂🧕ስለእኛ👳‍♂🧕

ሙሐመድ ነው!

የአዛቡ! የጀሒሙ! መጋረጃው፣
ለጀነቱ! የጉዞ ስንቅ! መነገጃው፣
የካኢኑ መደራጃው፣
የጁድ ኢንጃድ የማበጃው።

ሙሐመድ ነው!

በስሙ ነው ኦናው ዓለም የሚበራው፣
በስሙ ነው ስንኩሉ ቀን የሚደራው፣
በስሙ ነው ሐገር! ነገር! የሚገራው።

ሙሐመድ ነው!

መናገሻው መቋደሻ የራህመቱ፣
ከስሙ ጋር የተጠጋ
ምሶሶ ነው ለፍጥረቱ።

ሙሐመድ ነው!

ኮልኳይ ሸውቁን እየዘራ፣
ያህባቡን ሩህ ለጀዝቢያ የሚጠራ።
የፍቅሩ ቃል!
በዳበሳ ግዑዛን ላይ የሚጋባው፣
ቢናፍቀው!
ደረቅ ጉቶ አተለየኝ! ሲል ያስነባው፣
በረገጠው አሸዋ ላይ
ከግሮቹ ስር የሁቡ ጠጅ የሚፈሰው፣
አፈሩ እንኳን! ተመለስ ሲል!
እርገጠኝ ሲል! የሚያለቀሰው፣
ኸልቁን ሁላ ኢለየ ሲል ወሰወሰው፣
የሱካራ ብርሌ ነው የደገሰው፣
አልተረፈም ከዚያ ቅጂ የቀመሰው።

ሙሐመድ ነው!

የላሁቱ ምስጢር ቅኔ ያልተፈታው፣
የጀበሉት ሲር አስራሩን የሚፈታው፣
የናሱቱ ሽሽግ ግምጃ፣
የረሓሙት ድብቅ ሓጃ፣
የኻሊቁ እንደራሴ መቃረቢያ መወዳጃ።

ሙሐመድ ነው!

በሙሒቦች ዳዒም ስሙ የሚዘከር፣
ሲራ ቂሷው በየ ኸልዋው የሚመከር፣
የናፈቀው ከነበልባል የሚነከር፣
ስሙ’ንደ ኸምር ተጠጥቶ የሚሰከር።

ሙሐመድ ነው!

ጠያር ሸውቁ ወዳጆቹን ያስረገደው፣
አሽከሮቹን ወደ ሐድራው ያስማለደው።
ጁንዱን ኹላ ወደ ረውዷው ያስመነነ፣
ራብ ጥማት ነው ያልተገታ ያልሰከነ።

ሙሐመድ ነው!

ሙሓባ ነው!
ናፍቆትም ነው!
ውስዋስም ነው ያልታገደ።
ሙሒቦቹን እንደ ስለት እያረደ፣
ናፋቆቹን እንደ ሰደድ ያነደደ፣
ሚፋጅ እሳት ያልበረደ።

ሙሐመድ ነው!

በቡራቁ እርካብ ረግጦ የጋለበው፣
በጢባቁ ሁጁባቱን የገለበው።
የግሩ ኮቴ መላዒካን ያታለለው፣
ከውኑ ኹላ ወዳለበት የዋለለው።

ሙሐመድ ነው!

የረፍረፉን ደጀ ሰላም የጨለጠው፣
በጀላላው በኑር ሐገር የሰመጠው፣
ያርሹን ንጣፍ ከነ ጫማው የረገጠው፣
ሐድረተሏህ!
ጉዝጓዙ ላይ!
እንደቤቱ የቀበጠው።
………………………
( አለይሂ አፍዶሉ ሰላት ወአዝካ ተስሊም)

Zahi … 2014