Get Mystery Box with random crypto!

➽, ኢየሱስ ክርስቶስ የተከበረ ነብይና መልክተኛ ለመሆኑ #እሱ ግን #ነብይ ይሆን ዘንድ ይነ | 🍂 ረውደቱል ኢስላም የቁርአን እና የተርቢያ ማዕከል 🌿

➽, ኢየሱስ ክርስቶስ የተከበረ ነብይና መልክተኛ ለመሆኑ

#እሱ ግን #ነብይ ይሆን ዘንድ ይነቅል ዘንድ ያጠፋም ዘንድ እንደዚሁ ይተክል ዘንድ ይሠራም ዘንድ #በናቱ #ማኅፀን #ተመረጠ። (ሲራክ 49-7)
https://t.me/LAILAHA_ILELLAH_ISLAMIC
የዮሐንስ ወንጌል 13 : 20 - ፤ እውነት እውነት እላችኋለሁ፥ ማናቸውን የምልከውን የሚቀበል እኔን ይቀበላል፥ እኔንም የሚቀበል #የላከኝን ይቀበላል።

የዮሐንስ ወንጌል 12 : 44 - ፤ ኢየሱስም ጮኸ፥ እንዲህም አለ። በእኔ የሚያምን #በላከኝ ማመኑ ነው እንጂ በእኔ አይደለም፤

የዮሐንስ ወንጌል 14 : 24 - ፤ የማይወደኝ ቃሌን አይጠብቅም፤ የምትሰሙትም ቃል #የላከኝ የአብ ነው እንጂ የእኔ አይደለም።

የዮሐንስ ወንጌል 20 : 21 - ፤ ኢየሱስም ዳግመኛ። ሰላም ለእናንተ ይሁን፤ አብ እንደ #ላከኝ እኔ ደግሞ እልካችኋለሁ አላቸው።

የዮሐንስ ወንጌል 16 : 5 - ፤ አሁን ግን ወደ #ላከኝ እሄዳለሁ ከእናንተም። ወዴት ትሄዳለህ? ብሎ የሚጠይቀኝ የለም።

የሉቃስ ወንጌል 9 : 48 - ፤ ማንም ይህን ሕፃን በስሜ የሚቀበል እኔን ይቀበላል፤ የሚቀበለኝም ሁሉ #የላከኝን ይቀበላል፤ ከሁላችሁ የሚያንስ እርሱ ታላቅ ነውና አላቸው።

የዮሐንስ ወንጌል 15 : 21 - ፤ ዳሩ ግን #የላከኝን አያውቁምና ይህን ሁሉ ሰለ ስሜ ያደርጉባችኋል።

የዮሐንስ ወንጌል 12 : 49 - ፤ እኔ ከራሴ አልተናገርሁምና፤ ነገር ግን #የላከኝ አብ እርሱ የምለውን የምናገረውንም ትእዛዝ ሰጠኝ።

የዮሐንስ ወንጌል 9 : 4 - ፤ ቀን ሳለ #የላከኝን ሥራ ላደርግ ይገባኛል፤ ማንም ሊሠራ የማይችልባት ሌሊት ትመጣለች።

የዮሐንስ ወንጌል 8 : 42 - ፤ ኢየሱስም አላቸው። እግዚአብሔርስ አባታችሁ ከሆነ በወደዳችሁኝ ነበር፤ እኔ ከእግዚአብሔር ወጥቼ መጥቻለሁና፤ እርሱ #ላከኝ እንጂ ከራሴ አልመጣሁምና።

ሉቃስ 24:19
እርሱም (ኢየሱስም) ይህ ምንድነው? አለቸው
እነርሱም እንዲህ አሉት #በእግዚአብሔርና #በህዝቡ ሁሉ ፊት በስራና በቃል ብርቱ #ነብይ ስለነበረው ስለ ናዝሬቱ ስለ ኢየሱስ።

የዮሐንስ ወንጌል 4 : 34 - ፤ ኢየሱስም እንዲህ አላቸው። የእኔስ መብል #የላከኝን ፈቃድ አደርግ ዘንድ ሥራውንም እፈጽም ዘንድ ነው።

የዮሐንስ ወንጌል 8 : 29 - ፤ #የላከኝም ከእኔ ጋር ነው፤ እኔ ደስ የሚያሰኘውን ዘወትር አደርጋለሁና አብ ብቻዬን አይተወኝም አላቸው።

የዮሐንስ ወንጌል 8 : 26 - ፤ ስለ እናንተ የምናገረው የምፈርደውም ብዙ ነገር አለኝ፤ ዳሩ ግን #የላከኝ እውነተኛ ነው እኔም ከእርሱ የሰማሁትን ይህን ለዓለም እናገራለሁ አላቸው።

https://t.me/LAILAHA_ILELLAH_ISLAMIC
https://t.me/LAILAHA_ILELLAH_ISLAMIC