ጥያቄ ለክርስቲያን ወገኖች እንደሚታወቀው ትክክለኛው #አምላክ_ሁሉን_አዋቂ_ነው። የትኛውም አማኝ በዚህ ሀሳብ 100% ይስማማል እናም ጥያቄዬን እንደሚከተለው አቀርባለሁ። ኢየሱስ ክርስቶስ አምላክ ከሆነ ታድያ ኢየሱስ በራሱ አንደበት ለምን እንዲህ አለ? ኢየሱስ እንዲህ አለ:– ““ነገር ግን ስለዚያች ቀን ወይም ስለዚያችም ሰዓት #ከአብ #በቀር፣ የሰማይ መላእክትም ቢሆኑ፣ #ወልድም ( #ኢየሱስም ) ቢሆን፣ #ማንም_አያውቅም።” [— የማርቆስ ወንጌል 13፥32] ዮሐንስ ወንጌል 5:30 ኢየሱስ እንዲህ አለ:— "እኔ ከራሴ አንዳች ላደርግ አይቻለኝም፤ እንደ ሰማሁ እፈርዳለሁ ፍርዴም ቅን ነው፥ የላከኝን ፈቃድ እንጂ ፈቃዴን አልሻምና። ብሏል ኢየሱስ ክርስቶስ በራሱ አንደበት እንዲህ አለ:– " #አብ ( #እግዚአብሄር ) ሲያደርግ ያየውን ነው እንጂ #ወልድ ( #ኢየሱስ ) ከራሱ ሊያደርግ ምንም አይችልም።፤ (ዮሐንስ 5:19-20) ኢየሱስ ክርስቶስ በሌላ ቦታ ላይ በራሱ አንደበት እንዲህ አለ:– #ከራሴ _አንዳች_እንዳላደርግ በዚያን ጊዜ ታውቃላችሁ። (ዮሐንስ ወንጌል 8:28) የሚገርመው ግን አምላክ የተባሉት ኢየሱስ ክርስቶስ ስለሚመጣው ነገር ወይም ስለወደፊቱ ምንም #አላውቅም ማለቱ ነው። ማቲዮስ ወንጌል 24፥36 ይላል። እነዚህ 5 አንቀፆች ላይ ጥያቄዎች አሉን:– #1ኛ ወልድ (ኢየሱስ) አምላክ ከሆነ እና ከአብ (ከእግዚዘብሄር) ጋር እኩል ስልጣን አለው ከተባለ እንዴት ወልድም (ኢየሱስም) አያውቅም አብ (እግዚአብሄር) ብቻ ነው ሚያውቀው ሊል ቻል ? #2ኛ ብዙዎች ወልድ (ኢየሱስ) ያላወቀው እኮ #በስጋው_ነው ይሉናል። ታዲያ #እውቀት_የስጋ_ባህሪ_ነውን ? #3ኛ ወልድ (ኢየሱስ) በስጋው ከሆነ ያላወቀው መንፈስ ቅዱስስ በምኑ ነው ያላወቀው? ምክንያቱም ቃሉ የሚለው #ከአብ_በቀር_ማንም_አያውቅም ስለሚል ይህም ማለት በአጭሩ ወልድ(ኢየሱስ) እና መንፈስ ቅዱስ (ሰራፂ) በጭራሽ አያውቁም ነገር ግን አብ (እግዚአብሄር) ግን ብቻውን ያውቃል ማለት ነው። #4ኛ አብ (እግዚአብሄር) ወልድ (ኢየሱስ) መንፈስ ቅዱስ (ሰራፂ) በስልጣን በመለኮት በአገዛዝ እኩል ናቸው የሚል ትምህርታቹን ውድቅ አያደርገውም ወይ? ምክንያቱም አንዱ የሚያውቀውን ሌላው አያውቅምና ታድያ እንዴት #ስላሴ ((1+1+1= 1 ( አንድ ናቸው ማለት ይቻላልን ?) መልስ በማስረጃ https://t.me/LAILAHA_ILELLAH_ISLAMIC https://t.me/LAILAHA_ILELLAH_ISLAMIC 497 viewsedited 18:00