Get Mystery Box with random crypto!

“ሶላቱል ኢስቲኻራ” ማለት ምን ማለት ነው? @LAILAHA_ILELLAH_ISLAMIC @LAILAHA | 🍂 ረውደቱል ኢስላም የቁርአን እና የተርቢያ ማዕከል 🌿

“ሶላቱል ኢስቲኻራ” ማለት ምን ማለት ነው?

@LAILAHA_ILELLAH_ISLAMIC
@LAILAHA_ILELLAH_ISLAMIC

“ኢስቲኻራ” ማለት፡- ሁለት ነገራት አጣብቂኝ ውስጥ ከተውን፡ ወደየት ማዘንበልና ውሳኔ መስጠት አቅቶን በሚቸግረን ወቅት፡ ጌታችን አላህ በሁሉን ዐዋቂነቱ ለኛ የተሻለውን ይመርጥልንና ያመላክተን ዘንድ፡ እንዲሁም ያመላከተንን ነገር እንድንፈጽመውና እናገኘው ዘንድ እርዳታውን በመሻት የሚከወን የሶላት አይነት ነው፡፡ ይህ ሰጋጅ ሙስሊም፡ ውጤቱን በህልሙ ሊያየው ይችላል፡፡ ወይንም በሀሳቡ ወደተሻለው ነገር እንዲያጋድል አላህ ልቡን ይመራዋል፡፡ መንገዶቹ እጅግ ብዙ ነውና፡፡

ሰላት አል-ኢስቲኻራ አንዴት ይሰገዳል? ምን አይነት ዱዓ ነው የሚደረገው?

:- በሸሪዓው የተቀመጠውና ነቢዩ ሙሀመድ (ሰ.ዐ.ወ) ያስተማሩት ኢስቲኻራ ሰላት ሁለት ረከዓ ሰላት እነድነሰግድና ከዚያም የሚታወቀውን ዱዓ እንድናደረግ ነው ። እርሱም:-

اللهم إنى أستخيرك بعلمك ، وأستقدرك بقدرتك ، وأسألك من فضلك العظيم ، فإنك تقدر ولا أقدر ، وتعلم ولا أعلم ، وأنت علام الغيوب ، اللهم إن كنت تعلم أن هذا الأمر خير لى فى دينى ومعاشى ، وعاقبة أمرى ، وعاجله وآجله ، فاقدره لى ، ويسره لى ، ثم بارك لى فيه ، وإن كنت تعلم أن هذا الأمر شر لى فى دينى ، ومعاشى وعاقبة أمرى ، وعاجله وآجله ، فاصرفه عنى ، واصرفنى عنه ، واقدر لى الخير حيث كان ، ثم رضنى به ثم تسمى حاجتك

“አላህ ሆይ! በእውቀትህ አስመርጥሀለሁ፣ በችሎታህ ልቅና እንድታደረግልኝ እማፀንሀለሁ፣ ከታላቁ ችሮታህ እጠይቃሀለሁ። አንተ በችሎታህ ነገሮች እንዲከሰቱ ታደረግለህ፤ እኔ ግን አልችልም። አንተ ሁሉን ነገር ታውቃላህ፣ እኔ ግን (ምንም) ነገር አላውቅም። አንተ የሩቅ ነገሮችን ታውቃለህ። አላህ ሆይ! ይህ ጉዳየ ለዲኔና ለኑሮየ ለመጨረሻ ጉዳየ፣ ለቅርብም ሆነ ለሩቁ፣ ለአሁንም ሆነ ለወደፊቱ መልካም ከሆነ ለኔ እንዲፈፀም አድርገው፤ አግራልኝም፣ ከዚያም ባርክልኝ። አላህ ሆይ! ይህ ጉዳየ ለዲኔና ለኑሮየ፣ ለመጨረሻ ጉዳየ፣ ለቅርብም ሆነ ለሩቁ፣ ለአሁንም ሆነ ለወደፊቱ የሚጎዳኝ ከሆነ፣ ዘወር አድርግልኝ፣ እኔንም ከርሱ ዘወር አድርገኝ። መልካሙን ነገር የትም ቢሆን ለኔ ወስንልኝ። ከዚያም ውሳኔውን ወድጄ እንድቀበለው አድርገኝ። ከዚያም ሀጃህን (ጉዳይህን) ትናገራለህ (ትገልፃለህ)።”

ይህን ዱዓ ካደረግክ በኋላ ልብህ ክፍት የሆነበትን (ያዘነበለበትን) አቋም አላህ ላንተ የፈለገልህ ነው። ኢስቲኻራ ሰላት የሚሰገደው አሻሚና እኩል ደረጃ ባላቸው ጉዳዮች ላይ ነው። አንዱን በእርግጠኝነት ለመምረጥ በሚቸገርባቸው ሁኔታዎች ነው። በዚህ መሰረት በሸሪዓው በግልፅ የተቀመጡ ጉዳዮች ላይ ኢስቲኻራ አይሰገድም። አንድ ሙስሊም ያልሆነ ሰው ልጅህን ላግባ ተብሎ ለተጠየቀ ሰው ቆይ ኢስቲኻራ ልስገድና እወስንበታለሁ አይባልም። መጀመሪያ ጉዳዩ በዲን መስፈርት ለምርጫ መቅረብ የሚችል መሆን አለበት። ከዚያ በኋላ ነው ስለ ኢስቲኻራ ሊወራና ሊታሰብ የሚችለው። ለምሳሌ ሁለት በዲናቸው መልካም የሆኑ ሰዎች ለጋብቻ ልጁን ቢጠይቁት ለማን መዳር እንዳለበት ለመወሰን ኢስቲኻራ ሊሰግድ ይችላል። አላህም መልካሙን ይመርጥልታል።
@LAILAHA_ILELLAH_ISLAMIC
@LAILAHA_ILELLAH_ISLAMIC

አላህ ባነበብነው ምንጠቀም ያድርገን