Get Mystery Box with random crypto!

♡ቅን ልቦች♡

የቴሌግራም ቻናል አርማ kn_lboch — ♡ቅን ልቦች♡
የቴሌግራም ቻናል አርማ kn_lboch — ♡ቅን ልቦች♡
የሰርጥ አድራሻ: @kn_lboch
ምድቦች: ያልተመደበ
ቋንቋ: አማርኛ
ተመዝጋቢዎች: 644
የሰርጥ መግለጫ

#ቅን_ልቦች
" ወደ ውስጥህ በጥልቀት ቆፍር .....መቆፈርህን ከቀጠልክ ለመፍሰስ የተዘጋጀ የመልካምነት ምንጭ ታገኛለህ "
ወደ ውስጥ በጥልቅ የምንቆፍረው እንዴት ነው ???
መቆፈርስ ችላቹሃል ???
ይቀላቀሉን
⇩👇👇👇
@kn_lboch 👈አሁኑ ይቀላቀሉን
@kn_lboch
@kn_lboch
@kn_lboch
ሀሳብ👇👇
@Esmaelhabeshy

Ratings & Reviews

1.00

2 reviews

Reviews can be left only by registered users. All reviews are moderated by admins.

5 stars

0

4 stars

0

3 stars

0

2 stars

0

1 stars

2


የቅርብ ጊዜ መልዕክቶች 2

2022-03-17 23:19:22 "ዳርቻውን ብቻ አይተህ ሙሉ ባህርን መውደድ አትችልም።ወደ ጥልቀቱ ክፍል መግባት አለብህ።ማዕበል ወጀቡ ሊመታህ ይገባል።የፅልመት ክፍሉን ማየት አለብህ...ስቃዩን ልትዳብስ፤ቁጣውን ልታይ ይገባል።
ከዚያ በኃላ ወይ ሙሉውን ትወደዋለህ፤ወይ ሙሉውን ትጠላዋለህ፤ወይንም ሙሉውን ትተወዋለህ።
...ትክክለኛው ውዴታ የሚጀምረው የጋለ ስሜት ሲያልቅ ነው።"

@kn_lboch
457 views@EsmaelHabeshy, 20:19
ክፈት / አስተያየት ይስጡ
2022-03-09 22:20:05 ትምህርት ለዕውቀት ያዘጋጃል እንጂ ዕውቀትን አይጨርስም ። ዕውቀትህን የምትይዝበትን ሥነ-ሥርዓት ግን ያሳይሃል ። አእምሮህን ለማረቅ ትምህርት ፣ ሰውነትህን ለመግዛት ትዕግስት ፣ ከማንም ጋር ለመኖር ሥነ-ሥርዓት ያስፈልግሃል ። ለህሊናህ እረፍት ግን እምነት ያሻሃል ። ተከታይ ለማበጀት ደግሞ ግልጽ መሆንና ታማኝነት ግድ ይልሃል ።

አንተው እውነትን ጠልተሃት ዘመኑ እውነትን ጠልቷል አትበል ። ዘመን እኔና አንተ ነን ፤ በራሱ ክፉና ደግ የሆነ ዘመን የለም ።

@kn_lboch ይቀላቀሉን ሼር
942 views@EsmaelHabeshy, 19:20
ክፈት / አስተያየት ይስጡ
2022-03-08 00:02:18 ዘግይቶም ቢሆን የሚገባህ እውነት ነገሮችን በውድና ርካሽ የሚፈርጀው አስተሳሰብ እንጂ የነገሩ ወሳኝነት አለመሆኑ ነው። እርግጥ ማሕበረሰባዊ ስምምነቶች ለተፈጥሮ ህግ ከመገዛት ይልቅ መንጋነትን ያበረታሉ...ለምሳሌ:-

ዋናው ቁምነገር አብሮነትና ፍቅሩ ቢሆንም ውዱ ግን ሰርጋችን ነው...
ትልቁ እውቀት ራስን ማወቅ ቢሆንም ውዱ ግን ከአስኳላ የምንገዛው ነው።
ጠቃሚው ውበት ጸጥታ ቢሆንም የምንከፍለው ግን ለሚበጠብጠን ጩኸት ነው።
ጤናችን ያለው ንጹህ ውሃ ውስጥ ቢሆንም ብዙ የምንከፍለው ግን ለመታመሚያችን መጠጥ ነው...

@kn_lboch shr join
1.2K views@EsmaelHabeshy, edited  21:02
ክፈት / አስተያየት ይስጡ
2022-03-08 00:02:18 የሰው ልጅ ቆሞ ማሰብ እንዳለበት ማመኑ በጣም ትልቅ ነገር ነው፤ ነገር ግን ማወቅ ያለበት ነገር ቢኖር ቆሞ ማሰብ መጀመሩን ነው!

(ለአንዳንድ ቆመው ማሰብ ለፈለጉት)

@kn_lboch join
2.0K views@EsmaelHabeshy, edited  21:02
ክፈት / አስተያየት ይስጡ
2022-03-08 00:02:17 ''ተፈጥሮ በአእምሯችን ውስጥ በቀላሉ የማይረሳ እውነትን የሚናፍቅ ተክል ተክላለች''

@kn_lboch join
475 views@EsmaelHabeshy, edited  21:02
ክፈት / አስተያየት ይስጡ
2022-03-08 00:02:17 " ስህተት መስራት ሰዋዊ ነው ፤ በስህተት መጽናት ግን ድድብና ነው ። "

የሰው ልጅ አካባቢውን ይመስላል የሚባለው ስህተት ነው ። አካባቢው ነው የሰውን ልጅ የሚመስለው ። የቆሸሸ አስተሳሰብ ከሌለህ ዙርያህ ሊቆሽሽ አይችልም ። የተሳሳተ ግንዛቤ ከሌለህ ሰው መሳሳቱን እያወቅህ ዝም ለማለት አትደፍርም ። ስህተት መስራትህን ተረድተህ ስህተትህን ለማረም ካልሞከርክ ወይ ስህተት መሆኑን አላመንክም ወይም በስህተትህ ለመቆየት ፈልገሀል ያ ደግሞ አለማሰብ ሳይሆን ድድብና ይባላል ።



ብዙ ሰዎችን በሕይወታችን አስተውለን ከሆነ ስህተታቸውን ከማመን እና ከማረም ይልቅ...እገሌም እኮ እንዲህ አርጓል እያሉ የነሱን ድክመት ከሌላ ሰው ጋር በማናፃፀር ጥፋታቸውን ለመሸፈን ሲማስኑ ይውላሉ ። የተሸፈነ ጥፋት ማለት ግን አንድ ቀን አይኑን አፍጦ የሚወጣ እንጂ...የቀረ ወይም የታረመ ስህተት ማለት አይደለም ።



በአስተሳሰብ ሆነ በምግባር በኩል ያሉብንን ክፍተቶችና ስህተቶች እናርማቸው እንጂ አንደብቃቸው ።

copy!

@kn_lboch shr
454 views@EsmaelHabeshy, edited  21:02
ክፈት / አስተያየት ይስጡ
2022-03-08 00:02:17 ይድረስ ለሰፊው ህዝብ
.
.
አንዳንዴ ከእርምጃ
መቆም ቁጭ ማለት እጅጉን ይፈጥናል
ውሉ ካልታወቀ
ከነፃነት ትግል ባርነት ይሻላል!!!

ስለዚህ ሰፊው ህዝብ

ከመሮጥህ በፊት መድረሻህን አስብ
በስሜት ተሳክረህ
ሽቅብ ወጣሁ ብለህ ቁልቁል እንዳትሳብ!!!

Copy!

@kn_lboch shr
397 views@EsmaelHabeshy, edited  21:02
ክፈት / አስተያየት ይስጡ
2022-03-08 00:02:17 ህይወት ሁሉንም አንድ ዓይነት በሆነ መንገድ የምታስተናግድ መድረክ አይደለችም። ካወቅነው ይልቅ የማናውቀው ብዙ ነው። ዐይነቱና መጠኑ ይለያይ እንጂ ሁሉም ሰው የራሱ ጉድለት አለው። ይሁንና ደስታ የምርጫ ጉዳይ በመሆኑ ሁሉም ሰው ግን በህይወቱ ደስተኛ አይደለም።

ይኸውልህ፤ ኤሊ ምን ዓይነት ሸክም እንደተሸከመች ካወቅክ ለምን በጥንቃቄ እንደምትራመድ አትጠይቅም። ከሚታየው ምቾት ባሻገር የማይታዩ ብዙ ሸክሞች፣ ከሚማርኩ ፈገግታዎች ጀርባ ብዙ የልብ ቁስልና ህመሞች እንዳሉ እወቅ። ከሩቅ ያማረ ኑሮ ሁሉ የስኬት ምልክት፣ ከውጭ የሚታይ አንጸባራቂ ነገር ሁሉ ወርቅ አይደለምና። ስለዚህ ያወቅነው 'ደስታውን' ሲሆን ያላወቅነው ደግሞ 'ጉድለቱን/ችግሩንና ድካሙን/' ነው።

@kn_lboch join
398 views@EsmaelHabeshy, edited  21:02
ክፈት / አስተያየት ይስጡ
2022-03-08 00:02:16 "መቀየር የማንችለውን ነገር መቀበል ማለት ተስፋ መቁረጥ ማለት ሳይሆን አቅማችንን የምንችለው ነገር ላይ ማዋል ማለት ነው::"

በፍፁም ተስፋ አትቁረጥ ግን አቅምህን የምትችለው ነገር ላይ አውለው!

@kn_lboch join
375 views@EsmaelHabeshy, edited  21:02
ክፈት / አስተያየት ይስጡ
2022-03-08 00:02:16 የጨለማን ውበት በጨለማ ሳይሆን በብርሀን አስተውለው!

(ከኛ ሰፈር ጨለማ የመነጨ)

@kn_lboch join
389 views@EsmaelHabeshy, edited  21:02
ክፈት / አስተያየት ይስጡ