Get Mystery Box with random crypto!

' ስህተት መስራት ሰዋዊ ነው ፤ በስህተት መጽናት ግን ድድብና ነው ። ' የሰው ልጅ አካባቢውን | ♡ቅን ልቦች♡

" ስህተት መስራት ሰዋዊ ነው ፤ በስህተት መጽናት ግን ድድብና ነው ። "

የሰው ልጅ አካባቢውን ይመስላል የሚባለው ስህተት ነው ። አካባቢው ነው የሰውን ልጅ የሚመስለው ። የቆሸሸ አስተሳሰብ ከሌለህ ዙርያህ ሊቆሽሽ አይችልም ። የተሳሳተ ግንዛቤ ከሌለህ ሰው መሳሳቱን እያወቅህ ዝም ለማለት አትደፍርም ። ስህተት መስራትህን ተረድተህ ስህተትህን ለማረም ካልሞከርክ ወይ ስህተት መሆኑን አላመንክም ወይም በስህተትህ ለመቆየት ፈልገሀል ያ ደግሞ አለማሰብ ሳይሆን ድድብና ይባላል ።



ብዙ ሰዎችን በሕይወታችን አስተውለን ከሆነ ስህተታቸውን ከማመን እና ከማረም ይልቅ...እገሌም እኮ እንዲህ አርጓል እያሉ የነሱን ድክመት ከሌላ ሰው ጋር በማናፃፀር ጥፋታቸውን ለመሸፈን ሲማስኑ ይውላሉ ። የተሸፈነ ጥፋት ማለት ግን አንድ ቀን አይኑን አፍጦ የሚወጣ እንጂ...የቀረ ወይም የታረመ ስህተት ማለት አይደለም ።



በአስተሳሰብ ሆነ በምግባር በኩል ያሉብንን ክፍተቶችና ስህተቶች እናርማቸው እንጂ አንደብቃቸው ።

copy!

@kn_lboch shr