በእርሱ ዘንድ ምንም ነገር:- ሊጠገን እስከማይችል ድረስ አይበላሽም: ሊገኝ እስከማይችል ድረስ አይጠፋም: ሊታደስ የማይችል እስኪሆን ድረስ አይበሰብስም: ሊነሳ እስከማይችል ድረስ አይሞትም: ተስፋ የሌለው እስኪሆን አይዘገይም:: ስለዚህ በእግዚአብሔር ዘንድ ተበላሽቶ የሚቀር: ጠፍቶ የሚያበቃ: በስብሶ የሚጣል: ሞቶ የሚቀበር: ዘግይቶ ጊዜው የሚያልፍ ጉዳይ ፈፅሞ አይኖርም:: እግዚአብሔር የጊዜም : የሁኔታም: የነገሮችም አምላክ ነውና:: የምናመልከው እርሱ ለሞተው ህይወት የሚሰጥ የሌለውንም እንዳለ እርጎ የሚጠራ አምላክ ነው ። 740 views03:00