Get Mystery Box with random crypto!

አንጉላላ ሰሚነሸ ኪዳነምህረት

የቴሌግራም ቻናል አርማ kidanemhretseminesh — አንጉላላ ሰሚነሸ ኪዳነምህረት
የቴሌግራም ቻናል አርማ kidanemhretseminesh — አንጉላላ ሰሚነሸ ኪዳነምህረት
የሰርጥ አድራሻ: @kidanemhretseminesh
ምድቦች: ያልተመደበ
ቋንቋ: አማርኛ
ተመዝጋቢዎች: 2.82K
የሰርጥ መግለጫ

በኪዳነምህረት ሁሉም መልካም ይሆናል

Ratings & Reviews

2.67

3 reviews

Reviews can be left only by registered users. All reviews are moderated by admins.

5 stars

1

4 stars

0

3 stars

0

2 stars

1

1 stars

1


የቅርብ ጊዜ መልዕክቶች 2

2021-12-25 10:02:37 ኪሩቤልና ሱራፌል ቅዱስ ቅዱስ የሚሉትን አምላክ እንደ እናት "እሹሩሩ" ብላ ያስተኛች እርስዋ ነበረች:: #ቅድስት_ሆይ_ለምኝልን
4.8K views£rm!¥as , 07:02
ክፈት / አስተያየት ይስጡ
2021-12-23 08:51:02 "አሁን እየጾምክ ነው? እስቲ ጾምህን በተግባር አሳየኝ? የቱን ሰራህ? ድሃውን ባየህ ጊዜ ምህረትን አሳየው። ጠላትህን ስታየው ታረቀው። ስኬታማ የሆነ ወንድምህን ስታየው አትቅናበት በመንገድ የምትሔድ ሴትን ስታይ ዝም በለህ እለፋት። በአጠቃላይ አፍህ ብቻ አይጹም ነገር ግን ዓይንህ፣ እግርህ፣ እጅህ ሁሉም አካልህ ይጹም። እጅህ ከመስረቅና ከስስት ይጹም፣ እግሮችህ ወደ ኃጢአት ከመጓዝ ይከልከሉ፣ አይኖችህም በሌሎች ሰዎች ውበት ላይ ተተክለው ከመዋል ይጹሙ።

አሁን ስጋ እየበላህ አይደለም አይደል? በዓይንህም መጥፎ ነገር አትመልከት፤ መስማትንም ጹም። የፈውስ ጾም ክፉን አለመስማት የሌሎችንም ስም አለማጥፋት ነው። አንደበትም ከክፉና ከአጸያፊ ንግግር ይጹም። የዶሮና የአሳ ስጋ ከመብላት እንከለከላለን ነገር ግን የወንድማችንን ስጋ ስናኝክና ስንበላ እንውላለን። የወንድሙን ስጋ የሚበላ ደግሞ የተረገመና አሳች ነው። ቅዱስ ጳውሎስ “ነገር ግን እርስ በርሳችሁ ብትነካከሱና ብትበላሉ እርስ በርሳችሁ እንዳትጠፋፉ ተጠንቀቁ” እንዳለን። ገላ.5:15

ሆዳችንን ከምግብ ብቻ ባዶ ማድረግ አይደለም። ነገር ግን ሁለንተና ሕይወታችንን ራሳችንንም የምንቆጣጠር እኛ ወደ መንፈሳዊ ነገሮች የምንመራ መሆን አለብን።"

(የቅዱስ ዮሐንስ በረከቱ ይደርብን ውርስ ትርጉም #መምህር_ንዋይ_ካሳሁን)
5.4K views£rm!¥as , 05:51
ክፈት / አስተያየት ይስጡ
2021-11-30 08:35:07
ይቺ የእግዚአብሔር ደጅ ናት ወደእርሷ ፃድቃን ይገባሉ
መዝ 117(118)÷20
5.0K views£rm!¥as , 05:35
ክፈት / አስተያየት ይስጡ
2021-11-29 21:50:07
ሰው ሁሉ እናታችን ፅዮን ይላል
መዝ 85÷5
ህዳር
እንኳን አደረሳችሁ
4.7K views£rm!¥as , 18:50
ክፈት / አስተያየት ይስጡ
2021-11-27 08:50:27
አንቺ ፅዮን ማርያም አክሱም ላይ ያለሽው
ፅላተ ሙሴን በጉያሽ የያዝሽው
በህዳር 21 ለክብርሽ ስትመጪ
ለኢትዮጵያ ሀገራችን መፍትሔሽን አምጪ
4.2K views£rm!¥as , 05:50
ክፈት / አስተያየት ይስጡ
2021-11-22 20:12:27 ቅዳሜ ህዳር 18 የማር ፀበል ይሰጣልና ላልሰሙ እንዲደርስ ሼር እናድርግ ሰሚነሽ ኪዳነምህረት ለደጇ ታብቃችሁ ለምስክርነትም ዓውደምህረት ላይ ታቁማችሁ
4.7K views£rm!¥as , 17:12
ክፈት / አስተያየት ይስጡ
2021-11-20 08:16:59
4.4K views£rm!¥as , 05:16
ክፈት / አስተያየት ይስጡ
2021-11-20 08:16:55 ሕዳር 12 ቀን ዓመታዊው የቅዱስ ሚካኤል በዓለ ንግሥ ነው ። እንኳን አደረሳችሁ ።

በዚች በተወደደችው ዕለት ቅዱስ ሚካኤል በትዕዛዘ እግዚአብሔር ባህረ ኤርትራን ለሁለት ከፍሎ ሕዝበ እስራኤልን አሻገረ ፥ ፈርዖንን ከነሠራዊቱ ያሰጠመበትና ለሰው ልጆች በአምላኩ ፊት ተንበርክኮ የሚለምንባት ቀን ናት ።

ቅዱስ ሚካኤል እስራኤላዊያንን ከግብፅ ያወጣ በሲና በርሃ መና እየመገበ ቀዝቃዛ ውኃ እያጠጣ ደመና ጋርዶ አርባ ዘመን ሙሉ የረዳና የጠበቀ ሲሆን በኋላም ምድረ ርስትን እንዲወርሱ የረዳ ነው ። ኢሳ 5፥14

ስለ ቅዱስ ሚካኤል ከብዙ በጥቂቱ

ቅዱስ ሚካኤል በኃይላትና በሱራፌል ላይ የተሾመ ሲሆን ኃይላት የተባሉት ሠራዊተ መላእክት ሠይፈ እሳት ይዘው የሚኖሩ ለተልዕኮ የሚፋጠኑ ናቸው ።

ሊቀ መላእክት ቅዱስ ሚካኤል በክንፎቹ ስመ እግዚአብሔር ተፅፎበት የሰማያውያን ፍጥረታት መላእክት አለቃ ሆኖ ለዘለዓለም ተሾሞአል ።
ቅዱስ ሚካኤል ለመላው የሰው ልጅ ጠባቂና ረዳት ነው ። በመሆኑም በብሉያትም ሆነ በሐዲሳት መፅሐፍት ስሙ ተገልፆ ተፅፎአል ። ኢያ. 5፥14 ዳን 12፥1 ይሁዳ 1፥9 ዘፀ 14፥14

ቅዱስ ዳዊትን ከአረመኔው ከጎልያድ እጅ ያዳነ ዳዊትም በልጅነት አቅሙ ለዚያውም በወንጭፍ ጎልያድን እንዲገለው ዳዊትን የረዳና የጎልያድን ኃይል የሰበረ ቅዱስ ሚካኤል ነው ።

ቅዱስ ሚካኤል ሕዝብና አገር ይጠብቃል ።

ቅዱስ ሚካኤል ቅዱስ ጴጥሮስን ከእሥር ቤት አውጥቶታል ። የሐዋ ሥራ 12፥1-15

ሰማዕቱ ቅዱስ ጊዮርጊስም ተገርፎ ሥጋው ተቆራርጦና ተገድሎ በገደል በተጣለ ጊዜ ከእግዚአብሔር ታዝዞ ከሞት ያስነሳውና ከገደል ያወጣው ቅዱስ ሚካኤል ነው ።

ቅዱሳን አበው ፃድቃን በርሃ ገብተው በበዓት ተከተው ዝጉሐዊ ሁነው ፈጣሪአቸው እግዚአብሔርን ደጅ ሲፀኑ እኩይ ዲያብሎስ ከአደረሰባቸው ፅኑ መከራና ፈተና የጠበቃቸው ቅዱስ ሚካኤል ነው ። እነዚህም እንጦንስ መቃርስ ከሀገራችንም አቡነ አረጋዊ አቡነ ተክለሃይማኖት ቅድስት ክርስቶስ ሠምራ የመሳሰሉትን ቅዱሳን በምናኔ ዘመናቸው ሁሉ ከመከራ ሥጋ ከሠይጣን ወጥመድ የጠበቃቸውና የረዳቸው ቅዱስ ሚካኤል ነው ።
ቅዱስ ሚካኤል ለክርስቲያኖች ሁሉ ምንግዜም ረዳትና ጠባቂ ነው ።

ሁላችንንም በአማላጅነቱ ይጠብቀን ።
4.3K views£rm!¥as , 05:16
ክፈት / አስተያየት ይስጡ
2021-11-02 09:39:52
4.3K views£rm!¥as , 06:39
ክፈት / አስተያየት ይስጡ