Get Mystery Box with random crypto!

ሕዳር 12 ቀን ዓመታዊው የቅዱስ ሚካኤል በዓለ ንግሥ ነው ። እንኳን አደረሳችሁ ። በዚች | አንጉላላ ሰሚነሸ ኪዳነምህረት

ሕዳር 12 ቀን ዓመታዊው የቅዱስ ሚካኤል በዓለ ንግሥ ነው ። እንኳን አደረሳችሁ ።

በዚች በተወደደችው ዕለት ቅዱስ ሚካኤል በትዕዛዘ እግዚአብሔር ባህረ ኤርትራን ለሁለት ከፍሎ ሕዝበ እስራኤልን አሻገረ ፥ ፈርዖንን ከነሠራዊቱ ያሰጠመበትና ለሰው ልጆች በአምላኩ ፊት ተንበርክኮ የሚለምንባት ቀን ናት ።

ቅዱስ ሚካኤል እስራኤላዊያንን ከግብፅ ያወጣ በሲና በርሃ መና እየመገበ ቀዝቃዛ ውኃ እያጠጣ ደመና ጋርዶ አርባ ዘመን ሙሉ የረዳና የጠበቀ ሲሆን በኋላም ምድረ ርስትን እንዲወርሱ የረዳ ነው ። ኢሳ 5፥14

ስለ ቅዱስ ሚካኤል ከብዙ በጥቂቱ

ቅዱስ ሚካኤል በኃይላትና በሱራፌል ላይ የተሾመ ሲሆን ኃይላት የተባሉት ሠራዊተ መላእክት ሠይፈ እሳት ይዘው የሚኖሩ ለተልዕኮ የሚፋጠኑ ናቸው ።

ሊቀ መላእክት ቅዱስ ሚካኤል በክንፎቹ ስመ እግዚአብሔር ተፅፎበት የሰማያውያን ፍጥረታት መላእክት አለቃ ሆኖ ለዘለዓለም ተሾሞአል ።
ቅዱስ ሚካኤል ለመላው የሰው ልጅ ጠባቂና ረዳት ነው ። በመሆኑም በብሉያትም ሆነ በሐዲሳት መፅሐፍት ስሙ ተገልፆ ተፅፎአል ። ኢያ. 5፥14 ዳን 12፥1 ይሁዳ 1፥9 ዘፀ 14፥14

ቅዱስ ዳዊትን ከአረመኔው ከጎልያድ እጅ ያዳነ ዳዊትም በልጅነት አቅሙ ለዚያውም በወንጭፍ ጎልያድን እንዲገለው ዳዊትን የረዳና የጎልያድን ኃይል የሰበረ ቅዱስ ሚካኤል ነው ።

ቅዱስ ሚካኤል ሕዝብና አገር ይጠብቃል ።

ቅዱስ ሚካኤል ቅዱስ ጴጥሮስን ከእሥር ቤት አውጥቶታል ። የሐዋ ሥራ 12፥1-15

ሰማዕቱ ቅዱስ ጊዮርጊስም ተገርፎ ሥጋው ተቆራርጦና ተገድሎ በገደል በተጣለ ጊዜ ከእግዚአብሔር ታዝዞ ከሞት ያስነሳውና ከገደል ያወጣው ቅዱስ ሚካኤል ነው ።

ቅዱሳን አበው ፃድቃን በርሃ ገብተው በበዓት ተከተው ዝጉሐዊ ሁነው ፈጣሪአቸው እግዚአብሔርን ደጅ ሲፀኑ እኩይ ዲያብሎስ ከአደረሰባቸው ፅኑ መከራና ፈተና የጠበቃቸው ቅዱስ ሚካኤል ነው ። እነዚህም እንጦንስ መቃርስ ከሀገራችንም አቡነ አረጋዊ አቡነ ተክለሃይማኖት ቅድስት ክርስቶስ ሠምራ የመሳሰሉትን ቅዱሳን በምናኔ ዘመናቸው ሁሉ ከመከራ ሥጋ ከሠይጣን ወጥመድ የጠበቃቸውና የረዳቸው ቅዱስ ሚካኤል ነው ።
ቅዱስ ሚካኤል ለክርስቲያኖች ሁሉ ምንግዜም ረዳትና ጠባቂ ነው ።

ሁላችንንም በአማላጅነቱ ይጠብቀን ።