Get Mystery Box with random crypto!

'ፈገግታሽ ያምራል..ግን ለምን ነው ሰው ምትርቂው? ፈጣሪ የፈጠረውን ፍጡር ትፈሪያለሽ እንዴ?..የ | ኹሉድ ✍️

"ፈገግታሽ ያምራል..ግን ለምን ነው ሰው ምትርቂው? ፈጣሪ የፈጠረውን ፍጡር ትፈሪያለሽ እንዴ?..የሁል ጊዜ የሰዎች አስተያየት ነው..አሉታዊ አስተያየቶች ቢያሰለቹም..አዎንታዊ አስተያየቶች ሲደጋገሙ ለዛ ነገር ያለንን ፍቅር ያሳድገዋል..ሳቄን እወደዋለሁ ..ብቸኝነቴንም አፈቅረዋለው..ለደቂቃም ብትሆን በስህተት ሳልፈግግ መታየትን አልሻም...ሳቄን ፈገግታዬን ሂጃቤ አድርጌዋለው..የሳቄ ሱሰኛ እንደመሆን እዳዳለው።
ታድያ ለዛም ነው ሰዎችን ምርቀው...ብቀርባቸው ንፁህ ፈገግታዬን ሳቄን ሚያሳድፉብኝ ይመስለኛል..እንደዚህ ማሰቤ ራስ ወዳድ ያስብለኛልን?እንጃ? ግን ደግሞ እውነት አለኝ እኮ..የኋላኛው ታሪኬ ዳና ለዚህ በቂ ምክንያት ይሆኑኛል..አዎ አይኔ እያየ ቀስ በቀስ የጨለመው ወገግ ብሎ የነበረው የቤተሰቦቼ ፈገግታ ለዚህ ምስክር ይሆኑኛል..በገዛ ዘመድ ጎረቤት የተገፋችው እናቴ ሰውን ገደብ አበጅቶ መቅረብን አስተምሮኛል..ከእራሷ አልፎ ለሌላው ተስፋን ሚያሰንቀው የእናቴ የየዋህነት ፈገግታን እንደድክመት ተጠቅመው ተስፋዋን ሲያከስሙበት አይቻለው..በበልቶ ካጅ ጎረቤት፣ያጎረሰ እጅን ነካሽ በሆኑት ዘመዶች፣ከፊት ስቆ ጀርባ ወጊ በሆኑት የስራ ባልደረባ ምክንያት ቆዝሞ የቀረው ንቁ እና ቀልጣፋው አባቴ ለዚህ ምስክር ይሆነኛል..አንገት ደፍታ የምትሄደው ተሸማቃ ሰው ቀና ብላ የማታየው ተጫዋች እና ውቧ እህቴ ለዚህ ምስክር ትሆነኛለች...ከሰው መቀላቀል ትቶ ቤት ተቀምጦ የሚውለው ተግባቢ የነበረው ወንድሜ ለዚህ ምስክሬ ይሆናል..አዎን እኔም እንደነሱ ሰውን ከልክ በላይ አምኜ  ከጀርባ ተወግቼ... ላላገግም እንድጎዳ፣ ላልሽር እንድቆስል፣የምወደውን ፈገግታዬን እንድነጠቅ አልፈልግም..እናም ተውኝ አትነካኩኝ ሁሉን በሆድ ይዞ በሩቁ መፈገግ ለኔ ተመችቶኛል..
ኹሉድ