Get Mystery Box with random crypto!

I wonder if I still ever cross your mind..ስለ እኔ ያለክ ሀሳቦች አሁንም | ኹሉድ ✍️

I wonder if I still ever cross your mind..ስለ እኔ ያለክ ሀሳቦች አሁንም በአንዳንድ እኩለ ሌሊትክ ላይ ከመጡብክ ብዬ.. አሁንም ትዝታዬ ለብዙ አመታት አብረን ከተጋራናቸው በርካታ ነገሮች እና ቦታዎች ጋር ካገናኘከው..አሁንም ድምፄን እና የእግሬን ኮቴ ከታወቀክ ብዬ..አስባለሁ..ግን በማንኛውም አጋጣሚ በአእምሮክ ከተሻገርኩ ቀስ በቀስ ወደ ደረትህ እየተሳበ የሚሄድ የሆነ የህመም ስሜት ይሰማሃል? እሺ እንያ አስከፊ የጸጸት ስሜቶች በተከታታይ ቆዳክ ውስጥ ሰርፀው እየገቡ ነው ግን..ቆይ እንያ ጊዝያቶች በምን አይነት መንገድ ጭንቅላትክን እየመቱክ ሊሆን ይችላል? እንደገና እኔን ለማየት፣እንደገና እኔን ለመንካት፣እንደገና እኔን ለመያዝ፣ከእኔ ጋር እንደገና ቃል ለመገባባት..እስኪያስፈልግክ ድረስ ከባድ የናፍቆት ስሜት ይሰማሃል እንዴ?

Because I still do.
ከነዚህ ሁሉ አመታት በኋላም እኔን ይሰሙኛል .
ኹሉድ