Get Mystery Box with random crypto!

​••○● ተጎዳሁ ላንች ስል ●○•• ፍቅርዬ የኔ አለም ተጎዳሁ ላንቺ ስል፣ ጉንፍን እንደያዘው | ✮ً ̰̰̰̰̰̰̃̃̃̃̃̃ከዚህም ከዚያም TUBE✮ًٍٜ͜͡

​••○● ተጎዳሁ ላንች ስል ●○••

ፍቅርዬ የኔ አለም ተጎዳሁ ላንቺ ስል፣
ጉንፍን እንደያዘው በፍቅርሽ እስክስል፣
ብቻውን አንደቀረ በምድረ በዳ ላይ፣
ካንቺ በቀር ሌላ አይኔ ከቶ ሳያይ።
አፌም ውሎ አያቅም ስምሽን ሳይጠራ፣
ትሰሚኝ ይመስል ስላንቺ ሳወራ።

አንቺ ግድም የለሽ ቀልብሽ ከሌላ ነው ፣
ታዲያ የማተይኝ የማትርቂኝ ምነው ፣
በቅናት አይቼሽ የምብሰለሰለው፣
ፍቅርሽ ያነደደኝ ሳያንሰኝ ቀርቶ ነው።
ምን አለ የኔ ውድ ባየሽው የውስጤን፣
ባንቺ አደለም ወይ ያጣሁት እራሴን።
አይቶ እንዳላየ ለማለፍ ሳስመስል ፣
ብታይ ስንት ጊዜ ተጎዳሁ ላንቺ ስል።



━━━━⸙ ከዚህም ከዚያም⸙━━━━
▃▅▆██▆▅▃▃▅▆██▆▅▃