Get Mystery Box with random crypto!

​ ••○● ባል ትፈልጊያለሽ ●○•• ዳገቱን ሜዳውን የሂዎትን መንገድ ከጎንሽ ሳይለይ አብሮሽ የሚ | ✮ً ̰̰̰̰̰̰̃̃̃̃̃̃ከዚህም ከዚያም TUBE✮ًٍٜ͜͡

​ ••○● ባል ትፈልጊያለሽ ●○••

ዳገቱን ሜዳውን የሂዎትን መንገድ
ከጎንሽ ሳይለይ አብሮሽ የሚራመድ
ከልብ የሚያደምጥሽ
ክብር የሚሰጥሽ
ከሴትነት ወዲያ አስቦሽ እንደሚስት
ጊዜውን ስላንቺ የሚሰጥ ሳይሰስት
ለምቾት ድሎትሽ ሌተ ቀን የሚጥር
ህልሙን የሚያጋራሽ የኔነቱን ሚስጥር
አምረሽ ቆንጆ ሁነሽ በደስታ እንድትኖሪ
ከራሱ አስቀድሞ ላንቺ ተቆርቋሪ

ከባልንጀሮችሽ አንሰሽ እንዳትታይ
አሞላቆ ሚያኖር አድርጎ የበላይ
እንዳይስርድሽ ብሎ ቀድሞ እየተነሳ
እንዳይደክምሽ በሚል ላቅምሽ እየሳሳ
ቁርስ ሰርቶ አቅርቦ የሚቀሰቅሰሽ
ካልጋ ሳትወርጂ እዛው የሚያጎርስሽ
ጥፋት ስተትሽን እንዳላየ የሚያልፍ
ፍፁም የማይገኝ ከወቀሳ ደጃፍ
ቤተሰብ ዘመድሽን ካንቺ በላይ ወዶ
ቤተሰብ ዘመድሽን ካንቺ በላይ ወዶ
እናት የሚያደርግሽ ቆንጆ ልጆች ወልዶ

ሳል ትፈልጊያለሽ ፣
ንግሰት የሚያደርግሽ በደስታ ሚያኖርሽ
እንግዳስ አድምጭኝ ቁርጥሽን ልንገርሽ
ከጉድለት የፀዳ ሙሉ የሆነ ሰው
የለም አትሰስ ምኞቱም ዘሰት ነው
እናም አትድከሚ መስፈርት አትደርድሪ
ከነ እንከኑም ቢሆን ከሚወድሽ ኑሪ

አዎ ያ ነው ፍቅር አል
ከሺ ጥፋት ይልቅ አንድ ጥሩ ቆጥሮ
ከጎደሎ መሠል ሙሉ ነት አማትሮ
ከእኔ በፊት አስቀድሞ እኛነት
ተቻችሎ መኖር ኢጥብቦ ልዩነት
እናም ልድገምልሽ መስፈርት እትደርድሪ
ሙሉ ሰው ፍለጋ እድሜን እትቁጠረ
ከን እንከኑም ቢሆን ከሚወድሽ ጉረ


━━━━⸙ ከዚህም ከዚያምM⸙━━━━
▃▅▆██▆▅▃▃▅▆██▆▅▃