••○● ጥቂት ነው ምኞቴ ●○•• እኔ በህይወቴ ጥቂት ነው ምኞቴ ከድፍና ከግፍ የጠዳ ፡ በረንዳ እዚያ ላይ መቆየት ፥ ከሚደምን ዛፍ ላይ ፥ ቅጠል ሲዘንብ ማየት፤ አኔ በህይወቴ ጢኖ ነው ምኞቴ ለከርስ ጤፍ እንጀራ ለነፍስ ባለንጀራ ድክመቴን ስናዘዝ ፥ተግቶ ሚያዳምጠኝ በደሌን መዝኖ ፥ ቀኖና እማይሰጠኝ፤ እኔ በህይወቴ ጥቂት ነው ምኞቴ ሊሞላ የቃጣው፥ ደርበብ ያለ ኑሮ በስዊዝ ቤተ-ንዋይ፥ ሶስት መቶ ሺህ ዩሮ ደሞ ከተቻለ፥ ቆንጆ ሚስት ወይዘሮ እግዜርና ሰይጣን ፥ተጋግዘው የሳሏት ቢቻል ትንሽ ቪላ ፥አስር ክፍሎች ያሏት ግና ምኞቴ ሆይ ፥ እንዲያው ለመሆኑ ጥቂት ብሎ ነገር ፥ስንት ነው መጠኑ? ╔═══❖• •❖═══╗ @kezim_kezam ╚═══❖• •❖═══╝ 4 any comment @kezim_kezambot ❥❥__⚘_❥❥ 1.6K views̰̰̰̰̰̰̃̃̃̃̃̃ከዚህም ከዚያም TUßE✮ًٍٜ͜͡, 18:23