Get Mystery Box with random crypto!

​••○● ጥቂት ነው ምኞቴ ●○•• እኔ በህይወቴ ጥቂት ነው ምኞቴ ከድፍና ከግፍ የጠዳ ፡ | ✮ً ̰̰̰̰̰̰̃̃̃̃̃̃ከዚህም ከዚያም TUBE✮ًٍٜ͜͡

​••○● ጥቂት ነው ምኞቴ ●○••

እኔ በህይወቴ
ጥቂት ነው ምኞቴ
ከድፍና ከግፍ
የጠዳ ፡ በረንዳ
እዚያ ላይ መቆየት ፥
ከሚደምን ዛፍ ላይ ፥ ቅጠል ሲዘንብ ማየት፤

አኔ በህይወቴ
ጢኖ ነው ምኞቴ
ለከርስ ጤፍ እንጀራ
ለነፍስ ባለንጀራ
ድክመቴን ስናዘዝ ፥ተግቶ ሚያዳምጠኝ
በደሌን መዝኖ ፥ ቀኖና እማይሰጠኝ፤

እኔ በህይወቴ
ጥቂት ነው ምኞቴ
ሊሞላ የቃጣው፥ ደርበብ ያለ ኑሮ
በስዊዝ ቤተ-ንዋይ፥ ሶስት መቶ ሺህ ዩሮ
ደሞ ከተቻለ፥ ቆንጆ ሚስት ወይዘሮ
እግዜርና ሰይጣን ፥ተጋግዘው የሳሏት
ቢቻል ትንሽ ቪላ ፥አስር ክፍሎች ያሏት
ግና ምኞቴ ሆይ ፥ እንዲያው ለመሆኑ
ጥቂት ብሎ ነገር ፥ስንት ነው መጠኑ?



╔═══❖• •❖═══╗
@kezim_kezam
╚═══❖• •❖═══╝
4 any comment
@kezim_kezambot
❥❥__⚘_❥❥